ደረሰኝ ሳይዙ ሸቀጦችን ጭነው በሚንቀሳቀሱት ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው

Nested Applications

Asset Publisher

null ደረሰኝ ሳይዙ ሸቀጦችን ጭነው በሚንቀሳቀሱት ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው

የታክስ ሕጉ ማንኛውም ነጋዴ ወይም አገልግሎት ሰጪ ግብይት ካከናወነ በኋላ ደረሰኝ እንዲቆርጥ ቢያስገድድም ደረሰኝ የማይሰጡ እያጋጠሙ በመሆኑ የገቢዎች ሚኒስቴር እርምጃ ሊወስድ እንደሆነ በሚኒስቴር /ቤቱ የታክስ ማጭበርበርና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ገዙ አስታወቁ፡፡

አንድ ዕቃ ወይም አገልግሎት ሽያጭ በሚከናወንበት ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስን 15 በመቶ ጨምሮ ከገዢው ወይም ከተጠቃሚው ለመንግስት ታክስ እንዲሰበስብ በሕጉ ውክልና መሰጠቱን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡ ይሁንና በሀገራችን አገልግሎት ሰጪም ሆኑ በየደረጃው ያሉ የንግዱ ማህበረሰብ የታክስ ሕጉን ተከትለው እንደሚሠሩ ሁሉ ደረሰኝ የማይሰጡ መኖራቸውን አቶ ሲሳይ ጠቁመዋል፡፡

ከነዚህ መካከል ሸቀጦች እና ንብረቶች የሚያጓጉዙ እና ጫኝ ድርጅቶች መሆናቸውን ጠቅሰው ሸቀጥ ከመጫናቸው በፊት ሕጋዊ ሰነድ መኖርና አለመኖሩን እያረጋገጡ መሄድ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ይህንኑ ተቋሙ ወደ እርምጃ ከመግባቱ በፊት በማስታወቂያ እና በሌሎች የማስተማሪያ መንገዶች የማስገንዘብ ሥራ እንደሚሠራ አመልክተዋል፡፡ ሁሉም ክልሎች በዚህ ላይ በትኩረት እንዲሠሩ አቅጣጫ ለመስጠት መታሰቡን ጠቅሰው በየትኛውም ደረጃ ያሉ የሕግ አስከባሪ አካላት ጭነቶች በሚጓጓዙበት ጊዜ ህጋዊ ሰነድ መያዛቸውን እንዲያረጋግጡ እንደሚደረግም አብራርተዋል፡፡

በታክስ ሕጉ መሰረት አንድ ጭነት ሕጋዊ ሰነድ ሳይኖረው ሲንቀሳቀስ ከተያዘ በዋናነት የጭነቱ ባለቤት ሸቀጡን ከየት እንዳመጣ ማስረጃ መስጠት ያለበት ሲሆን ይህ ሳይሆን ሲቀር ወደ ኋላ በመሄድ ሸቀጡን ያለደረሰኝ የሸጠው አካል ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እና የሕግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትልበት አስታውቀዋል፡፡

Asset Publisher

ዜና

  • የገቢውን ዘርፍ ሁሉንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል Tue, 29 Oct 2024
የገቢውን ዘርፍ ሁሉንተናዊ እድገት ለማረጋገጥ ድጋፍና ክትትል ተደርጓል
  • የታክስ አሰባሰቡን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የባንኮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ Tue, 29 Oct 2024
የታክስ አሰባሰቡን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን የባንኮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

Nested Applications

Asset Publisher

.