በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል

Nested Applications

Asset Publisher

የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ Fri, 29 Mar 2024

በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል

በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል Mon, 18 Mar 2024

የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ

የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ Fri, 15 Mar 2024

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት Thu, 29 Feb 2024

Asset Publisher

null በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል

መጋቢት 07/2016 . (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉሙሩክ ኮሚሽን ከምሁራን እና ከቀድሞ የተቋም አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር  የምክክር መድረክ  አካሂዷል፡፡

መድረኩ የግብር ለሀገር ክብር ንቅናቄ አንድ አካል መሆኑን የገለፁት የገቢዎች ሚኒስትር / አይናለም ንጉሴ የታክስ ህግ ተገዥነትን ለማረጋገጥ እና ግብርና ታክስን በፈቃደኝነት የሚከፍል ማህበረሰብ ለመፍጠር የቀድሞ አመራሮች እና ሰራተኞች ሚናቸው የጎላ መሆኑን  ተናግረዋል::

በኦዲት፣ በኮንትሮባንድ መከላከል፣ በወጪና ገቢ ንግድ፣በሀሰተኛ ደረሰኝ ቁጥጥር እና በሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያላችሁ የካበተ ልምዳችሁ አሁን ላለነው የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ባለሞያዎች በእጅጉ   ያስፈልገናል ያሉት  ሚኒስትሯ በተለይ ምሁራን በጥናት እና ምርምር እንዲያግዙ እና የታክስ ሞራል ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የሚኒስቴሩ የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ / መሰረት መስቀሌ በበኩላቸው የቀድሞ አመራሮች፣ ሰራተኞች  እና ምሁራን የሀገር ሀብት መሆናቸውን ገልፀው በዘርፋ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ እና የተቋሙን የቀጣይ እቅድ አፈፃፀም በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ  ለማሳካት ከተቋሙ ጋር በቅርበት ስራዎችን ተናብቦ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

የቀድሞ አመራር፣ሰራተኞች እና ምሁራን ተቋሙን  ወደ ፊት ማሻገር እሚያስችል እምቅ አቅም ያላቸው በመሆኑ በታክስ እና ጉምሩክ ዙሪያ በግንዛቤ ስርፀት፣ ጥናት እና ምርምር በማካሄድ እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ድጋፍ እንዲያደርጉ የጠየቁት ደግሞ የጉምሩክ ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ናቸው፡፡

በመርሀ ግብሩ የሪፎርምና የታክስ ሕግ ተገዢነትን የተመለከቱ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል::

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

Nested Applications

Asset Publisher

.