ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ላሉ ዲያስፖራዎች ፈጣን አገልግሎት እየተሰጠ ነው

Nested Applications

Asset Publisher

የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ Fri, 29 Mar 2024

በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል

በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል Mon, 18 Mar 2024

የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ

የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ Fri, 15 Mar 2024

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት Thu, 29 Feb 2024

Asset Publisher

null ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ላሉ ዲያስፖራዎች ፈጣን አገልግሎት እየተሰጠ ነው

የጉምሩክ ኮሚሽን ከተለያዩ ዓለም ሀገራት ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ላሉ መንገደኞች የተለየ የጉምሩክ አገልግሎት መስጫ ቦታ በማዘጋጀት ፈጣን አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት የመንደገኞች ጉዳይ /ስራ አስኪያጅ አቶ ዘራኤል ለአ ገልፀዋል፡፡

የህክምና ቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎችን ይዘው የሚመጡ መንገደኞችም ያመጡትን ድጋፍ በቀላሉ ለማስረከብ እንዲያመቻቸው ከጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር እና መጋዘን በማዘጋጀት አገልግሎት እየተሰጠ እንደሆነ /ስራ አስኪያጁ አክለው ገልፀዋል፡፡

ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉ ዲያስፖራዎችን በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲሁም የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማዋቀር 24 ሰዓት ፈጣን አገልግሎት እየተሰጠ እንደሆነ የገለፁት ደግሞ የቅ//ቤቱ የኢንተርናሽናል መንገደኞች ቡድን አስተባበሪ አቶ ዝያድ ኑረታ ናቸው፡፡

ዲያስፖራዎች ወደ ኢትዮጵያ ይዘው የመጡትን የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች በህጋዊ መንገድ በመመንዘር ሀገራችን በቂ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ የበኩላቸውን አተዋፅኦ እንዲያበረክቱም ቡድን አስተባባሪው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ከአሜሪካ ኮሎንበስ ግዛት የመጡት ወ/ሮ ውበት በላቸው እና አቶ አጋር ወልዴ የተባሉ ዲያስፖራዎች በበኩላቸው በተደረገላቸው መልካም አቀባበልና ፈጣን የጉምሩክ አገልግሎት መደሰታቸውን ገልፀው በቆይታቸው የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጤን እና ኢንቨስት በማድረግ ሰፊ የስራ እድልን ለመፍጠር እምዲሁም ምርቶችን ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ ሀገራችን በቂ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ እንደሚሰሩም ጠቁመዋል፡፡

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

Nested Applications

Asset Publisher

.