በአምስት ወራት ውስጥ 126.85 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰበሰበ

Nested Applications

Asset Publisher

Asset Publisher

Asset Publisher

null በአምስት ወራት ውስጥ 126.85 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰበሰበ

ታህሳስ 5/2013 .

የገቢዎች ሚኒስቴር ሀገራዊ ወጪን በሀገራዊ ገቢ የመሸፈን ራዕይ አንግቦ የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እየሰራ ይገኛል፡፡ በበጀት ዓመቱ 290 ቢሊዮን ብር ለመስበሰብ የሚያስችሉ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመስራት ወደ ስራ የገባው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዕቅዱ በወር ከፋፍሎ ለቅርንጫፍ /ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት በማውረድ ጠንካራ የክትትልና ደጋፍ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ ዕቅዱን ተግባራዊ ማድረግ ሲጀመርም የዕቅድ አፈጻጸማቸው በክትትልና ድጋፍ መድረኮች በመገምገም ጠንካራ ጎኖች እንዲቀጥሉ እና ችግሮች እንዲቀርፉ የሚያስችሉ ስራዎችን በማከናወን የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ርብርብ ተደርጓል፡፡

ከክትትልና ድጋፍ ስራዎች ባሻገር የተሻለ የታክስ ህግ ተገዥነት ላሳዩ ግብር ከፋዮች እንዲሁም ስራቸውን በትጋት ለከወኑ አመራሮችና ሰራተኞች ዕውቅናና ሽልማት የመስጠት ስራ ተጠናክሮ በመቀጠሉ በግብር ከፋዮችና ሰራተኞች ውስጥ መነሳሳት በመፈጠሩ እና በአጋርነት ለመሰራት ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ የገቢ አሰባሰቡ ላይ በጎ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡

ሌላው የገቢ አሰባሰቡ ስራን የሚያቀላጥፍ፣ የግብር ከፋዮችን ጊዜ የሚቆጥቡ እና ወጪን የሚቀንሱ የኢታክስ፣ የጉምሩክ ወረቀት አልባ አገልገሎት እና የአንድ መስኮት አገልግሎት የመሳሰሉ በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሰራሮች ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ እነዚህን እና ሌሎች አጋዥ ስራዎችን በመስራት በተደረገ ርብርብ በያዝነው በጀት ዓመት ከሐምሌ እስከ ህዳር ባሉት አምስት ወራት ብቻ 126 ቢሊዮን 835 ሚሊዮን 480 ሺህ 740 ነጥብ 99 ብር በመሰብሰብ 101 በመቶ አፈፃጸም ተመዝግቧል፡፡ አፈፃፀሙ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 17.4 ቢሊዮን ብር በላይ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የገቢ ዓይነቶች ድርሻ ሲታይ ከአገር ውስጥ ገቢ 80.96 ቢሊዮን ብር፣ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 45.77 ቢሊዮን ብር እና ከሎተሪ ሽያጭ 109.45 ሚሊዮን ብር ነው፡፡

በኮቪድ ወረርሽኝ ተፅዕኖ እና ወቅታዊው የፀጥታ ችግር ውስጥ ከዕቅድ በላይ አፈፃፀም ማስመዝገብ በርካቶች ይሳካል ብለው የማይገምቱት ነው፡፡ ነገር ግን የግብር ከፋዮቻችን በፈቃደኝነት ግብር የመክፈል፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት እና የዘርፉ አመራሮችና ሰራተኞች የእርፍት ቀናት ጭምር ስራቸውን በትጋት በመስራታቸው ውጤታማ አፈፃፀም እንዲመዘገብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

ለዚህ ስኬታማ የገቢ አሰባሰብ ግብራችሁን በወቅቱ አሳውቃችሁ በመክፈል በአጋርነት ለሰራችሁ ግብር ከፋዮች ደንበኞቻችን ምስጋናችንን እያቀረብን በታህሳስ ወር 21.33 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቀደ በመሆኑ ይህን ዕቅድ ለማሳካትም እየተወጣችሁ ያላችሁትን ኃላፊነት አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ የገቢዎች ሚኒስቴር ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Our Services

የእኛ አገልግሎቶች

 

 

 

 

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

.