በጥቅምት ወር ከ53 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

2014 በጀት ዓመት በጥቅምት ወር 56ቢሊየን 588ሚሊየን 899 862ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 53ቢሊየን 906ሚሊየን 833 456ብር መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አቶ ላቀ አያሌው ገልጸዋል፡፡ አፈጻጸሙም 95.26 በመቶ ሆኗል፡፡

እቅድ አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የብር 9ቢሊዮን 657ሚሊየን 313 974ብር ወይም 21.82% ዕድገት ማሳየቱን የገለጹት ሚኒስትሩ አቶ ላቀ ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ ከሀገር ውስጥ ታክስ 42ቢሊየን 067ሚሊየን 793 289ብር፣ ከውጭ ንግድ ታክስና ቀረጥ 11ቢሊየን 839ሚሊየን 040 167ብር መሰብሰቡን አሳውቀዋል፡፡

አቶ ላቀ ገቢው በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት አራት ቅርንጫፎች ምንም ሳይሰሩ እንዲሁም በሌሎችም ቅርንጫፎች ቢሆን በተገደበ እንቅስቃሴ ውስጥ ሆኖ የተሰበሰበ በመሆኑ አፈፃፀሙ የተሻለ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

አፈጻጸሙ በዚህ ወቅት ግብር ከፋዮቻችን ብዙ ሰበቦችን ሳያቀርቡ ለአገራቸውና ለህዝባቸው በማሰብ በወቅቱና በትክክለኛው ጊዜ ግብራቸው አሳውቀው በመክፈላቸው እንዲሁም የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞችም እንኳን ጉልበት፣ እውቀት እና ጊዜ ሌላው ኢትዮጵያዊ ለአገሩ ህይወቱን እየሰጠ ነው በሚል መንፈስ ከምንጊዜውም በላይ የዕረፍት ጊዜአቸውን ጨምረው በመጠቀም እና የገቢ ምንጮችን በዝርዝር በማየት እንዲሁም በቁርጠኝነት እና በትጋት ከልብ መስራት በመቻላቸው የተገኘ ውጤት መሆኑን ገልጸው ሁሉንም ለአፈጻጸሙ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በገቢዎች ሚኒስቴር ስም ምስጋናዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ ብለዋል፡፡ በቀጣይም የተሻለ በመስራት አገራችንን ከዚህ ክፉ ጊዜ በጋራ እንድናሻግራት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)