"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው

በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት ከግብር ከፋዮችና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የካቲት 20/2013 ዓ.ም  ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው፤ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ሀሰተኛ ደረሰኝ ከመጠቀምና ሀሰተኛ ኪሳራ ከማሳወቅ በመቆጠብ ለታክስ ህግ ተገዢ በመሆን ዘመናዊ የንግድ ስርዓት በማስተዋወቅ የልዕቀት ማዕከል ሊሆኑ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በሰባት ወራት ውስጥ ከተሰበሰበው ጠቅላ ገቢ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ድርሻ 50 በመቶ ከሀገር ውስጥ ገቢ ደግሞ 80 በመቶ ድርሻ አለው ነው ያሉት፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም ከድህነትና ኋላቀርነት የተላቀቀች ሀገር ለመገንባት በገቢ ሰብሳቢ በኩል የሚስተዋለው የአሰራር ግድፈቶችን ማረም፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን፣ በደንበኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በቅንነት ተቀብሎ በማስተናገድ የገቢ መሰረትን ለማስፋት እንሰራለን ብለዋል፡፡

ግብር ከፋዮች ግብር መሰወርና ሸሽ ሀገራዊ ወጪ በሀገራዊ ገቢ የመሸፈን ራዕያችንን የሚያደናቅፍ በመሆኑ ግብር ከፋዮች ከዚህ ችግር እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የታክስ አማካሪነትና ጉዳይ አስፈጻሚነት እንደ ሽፋን በመጠቀም ግብር ከፋዮችን ወደ አልተገባ ድርጊት የሚወስዱ ህገወጦች በመኖራቸው የታክስ ህግ ተገዢነት እንዳይተገበር እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የከፍተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ታሬሳ እንሴሱ በበኩላቸው //ቤቱ በሰባት ወራት ውስጥ 79.98 ቢሊየን ብር በመሰብሰብሰብ የእቅዱን 108 በመቶ ማሳካቱን እንዲሁም በፌደራል ደረጃ ተሸላሚ ለነበሩ 150 ግብር ከፋዮች ልዩ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስማጭበርበርና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ገዙ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ከዕቅድ አንጻር የሚሰበሰበው ገቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገት ቢያሳይም ወጪን ከመሸፈን አንጻር የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡ 2012 በጀት ዓመት በታክስ ገቢ የሀገሪቱን 48 በመቶ ብቻ ወጪ እንደሸፈነና ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ገቢ 8.66 በመቶ ብቻ እየተሰበሰበ ሲሆን ለዚህም ዋነኛው ምክንያት የታክስ ህግ ተገዢነት ችግር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)