በሁሉም መስኮች የተከናወነው ሪፎርም ለተገኘው የገቢ ዕድገት ሚናው የጎላ ነው- አቶ ተስፋዬ ቱሉ የታክሰ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

የገቢዎች ሚኒስቴር በሰራቸው ትላልቅ የሪፎርም ስራዎች ሀገራዊ ገቢን ማሳደግ መቻሉን የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ቱሉ መጋቢት 21/2013 . ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለፃ ሚኒስቴር /ቤቱ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በሰራቸው የሪፎርም ስራዎች አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል፡፡ በተለይም ከዚህ በፊት ለስራው ደጋፊ ያልነበሩ አሳሪ መመሪያዎች የኤክሳይስ ታክስ አዋጅን ጨምሮ እንዲሻሻሉ መደረጋቸው፣ የታክስ መሰረቶች መስፋታቸው፣ የአደረጃጀት ክለሳ መደረጉና ሌሎች የሪፎርም ስራዎች ለገቢው ዕድገት ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት መዘርጋት፣ ግብራቸውን በወቅቱ አሳውቀው የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ቁጥር እያደገ መምጣት፣ የእረፍት ቀናት ለስራ በመጠቀም፣ የኮትሮባንድ የመያዝ አቅም ማደግ፣ ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱ፣ በግብር ከፋዮችና በተቋሙ መካከል ተቀራርቦ መስራት በመጀመሩ፣ ግብር ከፋዮችን እንደ ባህሪያቸው በመለየት የህግ ተገዥነት ስትራቴጂ ተግባራዊ በመደረጉ በተደጋጋሚ ለተመዘገበው ውጤታማ አፈፃፀም አስተዋፅኦ ማድረጉን አንስተዋል፡፡

ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ይነሱ የነበሩ ችግሮችን ለመቅረፍ የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ ናቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ተጨማሪ //ቤት እና የስራ ሂደቶችን በማደራጀትና አስፈላጊዉን የሰው ሀይል በመመደብ የተሻለ አፈፃፀም መታየቱን አመልክተዋል፡፡ ከግብር ከፋዮች ትምህርት ጋር በተያያዘም ሚኒስቴር /ቤቱ በትኩረት እየሰራ እንደሆነና ተጨባጭ ውጤት እየታየበት መሆኑን አውስተዋል፡፡

የገቢ አሰባሰቡን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የገለፁት አቶ ተስፋዬ በዚህም እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ በአዲስ አበባ ግብራቸውን የኢ-ፋይል ተጠቃሚ ግብር ከፋዮች 70% ለማድረስ እንዲሁም የኢ-ፔይመንት ተጠቃሚዎች 36% ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህም የገቢ አከፋፈልና አሰባሰቡን ቀልጣፋ፣ ቀላል፣ ዘመናዊ እና ጊዜ ቆጣቢ እንዲሆን በማድረጉ ረገድ የማይተካ ሚና አለው ብለዋል፡፡

በቀጣይም ዘመኑ የሚፈልገውን የቴክኖሎጂ አማራጭ በመጠቀም በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ልክ ገቢን ለመሰብሰብ በተለየ ትኩረት ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ በስምንት ወራት ሊሰበስበው ካቀደው 191.28 ቢሊየን ብር ውስጥ 191.45 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ጠቁመው በቀጣይም የገቢ ዕቅዱን ከማሳካት አንፃር ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Sat, 18 Sep 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • 10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል Thu, 22 Jul 2021
10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል