የገቢ አሰባሰቡን በሚጎዳ ህገ-ወጥ ተግባር ተሰማርተው የነበሩ 63 ህገ-ወጥ ድርጅቶች ተያዙ
የገቢ አሰባሰቡን በሚጎዳ ህገ-ወጥ ተግባር ተሰማርተው የነበሩ 63 ህገ-ወጥ ድርጅቶች ተያዙ
/የገቢዎች ሚኒስቴር/
የገቢዎች ሚኒስቴር ለአራት ወራት ባደረገው ምርመራ ከታክስ አስተዳደር ተሰውረው ሀሰተኛ ግብይት ሲያከናውኑ የነበሩ እና በህገ-ወጥ መንገድ የካሽሬጂስተር ማሽን ሲጠቀሙ የነበሩ ስልሳ ሶስት ድርጅቶች መያዝ ችሏል፡፡
በክትትል የተደረሰባቸው ህገ-ወጥ ድርጅቶች መከፈል የነበረበት ግብር እንዲሰወር በማድረግ በገቢ አሰባሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩ ሲሆኑ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሃያ ህገ-ወጥ የካሽ ሬጂስተር ማሽኖች ተይዘዋል፡፡
በህገ-ወጥ ተግባሩ ተሳትፎ ሊኖራቸው ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ ይገኛል፡፡
ዝርዝራቸው ከዚህ በታች ከተገለፁት ድርጅቶች ጋር ግብይት ያልፈፀማችሁ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ግብይት ፈፅማችሁ የተገኛችሁ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ድርጅቶቹን ኦዲት በማድረግ የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ ይወዳል፡፡
ሀገራቸውን የሚወዱ ከሰሩት ብቻ ሳይሆን ከራሳቸው ሳይሰስቱ በሚሰጡበት በዚህ ወቅት እንደዚህ ዓይነት ህገ-ወጥ ድርጅቶች ደግሞ ከእናት ሀገራቸው ይሰርቃሉ፡፡ ህዝባችን ከእናት ሀገራቸው የሚሰርቁ ድርጅቶችን ባለመታገስ ለሀገሩ በያገባኛል ስሜት መሳተፍ አለበት፡፡
በብዛት የተነበቡ ዜናዎች
-
Fri, 29 Oct 2021"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
-
Wed, 4 Jan 2023"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)