Asset Publisher

null ለሀገራችን በቁጭት ልንሰራ ይገባል! - ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር

በገቢዎች ሚኒስቴር አዘጋጅነት የ2016 በጀት ዓመት በፌዴራል፣ በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች መካከል ሲካሄድ የነበረው የጋራ የምክክር መድረክ ተጠናቋል፡፡

በጋራ የውይይት መድረኩ ላይ የአራት ወር ሀገራዊ የገቢ ዕቅድ አፈፃጸም ቀርቦ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን በቀጣይ ሀገሪቷ መሰብሰብ ያለባትን ገቢ መሰብሰብ እንዲቻል ሁሉም ክልል እና ከተማ አስተዳደር የገቢ አቅማቸውን በሚገባ በመፈተሽ ለመስራት መተማመን ላይ ደርሰዋል፡፡

በተጨማሪም ከገቢ ትልልፍ፣ ከጋራ ገቢዎች፣ ከንግድ ምዝገባ፣ የግብር እፎይታ፣ የካሽ ሬጂስተር ተደራሸነት፣ የደረሰኝ አጠቃቀም፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የታክስ ህግ-ተገዢነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመድረኩ ማጠቃለያ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ እንደ ሀገር ካቀድነው እቅድ አንፃር የገቢ አፈፃጸማችን ከፍተኛ መሆኑ የተገለጸ ቢሆንም ሀገሪቷ ማመንጨት ከምትችለው ገቢ አኳያ አፈጻጸሙ አናሳ መሆኑ ከግንዛቤ ገብቶ ለሀገራችን በቁጭት ልንሰራ እንደሚገባ እና ሁሉም በጋራ እና በተናበበ መልኩ ገቢን ለማሳደግ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

በሚኒስቴሩ የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተሰፋዬ ቱሉ ከቴክኖሎጂ ልማት ስራዎች ጋር ተያይዞ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በተለይ በቅርቡ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ /electronics invoice/ ለምቶ ወደ ሙከራ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በገቢው ዘርፍ ያለው መልካም የስራ ግንኙነት በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የጠቆሙት በሚኒስቴሩ የታክስ ኦፐሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ በገቢ ትልልፍ ላይ በቅርበት እና በመግባባት መሰራት አለበት ብለዋል፡፡ ለዚህም መረጃ በተገቢው ሁኔታ ተይዞ ጥቅም ላይ ሊውል ይገባል ያሉ ሲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ግንኙነት በእቅድ ሊመራ እንደሚገባ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በግብር አሰባሰቡ ሂደት የጋጠማቸውን ችግሮች አንስተው ውይይት ያካሄዱ ሲሆን የመፍትሄ ሀሳቦችም ቀርበዋል፡፡ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከውይይቱ ገንቢ እና ለቀጣይ ስራቸው የሚያግዝ ሀሳብና እና ልምድ ማግኘታቸውንም ተናግረዋል፡፡

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)