Asset Publisher

null ከታክስ እና ቀረጥ የሚገኘው ገቢ በየዓመቱ በአማካይ በ23.8 በመቶ እያደገ መምጣቱ ተገለጸ

በገቢዎች ሚኒስቴር አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው ሀገር አቀፍ የታክስ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የ2016 በጀት ዓመት በፌዴራል፣ በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች መካከል ዓመታዊ የታክስ የምክክር የጋራ ውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ከ2011 በጀት ዓመት ጀምሮ እንደሀገር ሀገራዊ ገቢ በአማካይ በ23.8 በመቶ እያደገ የመጣ ቢሆንም የታክስ ገቢ ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ጥምርታ አንጻር ሲታይ አነስተኛ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም የተለያዩ ተግዳሮቶች አሉ ብለዋል፡፡

በተለይ ለገቢ አሰባሰቡ ከፍተኛ እክል እየሆኑ ያሉ የሕገ-ወጥ ንግድ፣ ኮንትሮባንድ፣ ደረሰኝ ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እና መሰል ችግሮች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ ያሉት ሚኒስትሯ እነኚህን ችግሮች ለማስተካከል ብዙ ስራዎች መሰራት ያለባቸው ቢሆንም በዋነኝነት ግን የአሰራር ስርዓታችንን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግ ማጭበርበርን ለመከላከል ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡

የምክክር መድረኩ የፌደራል፣ የክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ታክስን በተመለከተ ልምድ የሚለዋወጡበት፣ አፈጻጸማቸውን የሚገመግሙበት፣ ሕገ-ወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድን ለመታገል አቅማቸውን የሚያድሱበት መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሯ በአጠቃላይ ሀገራዊ የታክ አስተዳደር እና ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ የጋራ አቋም እንደሚያዝ አሳውቀዋል፡፡

በምክክር መድረኩ የገቢዎች ሚኒስትር፣ የጉምሩክ ኮሚሽነር፣ የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ፣ ከየክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የገቢ እና የንግድ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች የስራ ኃላፊዎች እና ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)