በአዲሱ ኤክሳይስ ታክስ አዋጅ አተገባበር ዙሪያ ያለአግባብ እየተጨመሩ ያሉ ዋጋዎችን ሊያጠራ የሚችል ውይይት ከአምራቾች ጋር ተካሄደ፡፡

በአዲሱ ኤክሳይስ ታክስ አዋጅ አተገባበር ዙሪያ ያለአግባብ እየተጨመሩ ያሉ ዋጋዎችን ሊያጠራ የሚችል ውይይት ከአምራቾች ጋር ተካሄደ፡፡
….
ውይይቱ ከቢራ አምራቾች ጋር የተካሄደ ሲሆን የዋጋ ጭማሪና የሰራተኛ መቀነስ የውይይቱ አጀንዳዎች ናቸው ውይይቱንም የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤና የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በጋራ በምራት ከቢራ አመራቾች ለተነሱት ጥያቄና አስተያየት መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች መካከል የገብስ ዋጋ መጨመር በቢራ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉ አምራቾች እንደምክንያት ያቀረቡ ቢሆንም ከመድረክ በተሰጠው ምላሽ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተፈጠረ በመሆኑ ከአዋጁ ጋር ግንኙት እንደሌለው ተገልጾዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ሚዲያዎች የዋጋ ንረት ሊያስከትል የሚችል የታክስ አዋጅ እንደሆነ አድርገው ቀድመው በመስራታቸው ለዋጋ መጨመር መንስሄ እንደሆነና ከአምራቾች በኩል የቢራ ማሰታዎቂያ መከልከልና የተጠቃሚው ቁጥር መቀነስ ጋር ተያይዞ ለዋጋ መጨመሩ እንደምክኒያት ያነሱ ቢሆንም ይሄም ከአዋጁ ጋር እንደማይገናኝና በመንግስት በኩል የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ተገልጾዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በውይይቱ ወቅት፤ የኢትዮጵያ የታክስ ምጣኔ ከአፍሪካም ሆነ ከአለም ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ የታክስ ምጣኔ መሆኑን አንስተው፤ ሀገሪቱ ታክስ መሰብሰብ ብቻ ሳይሆን ለፋብሪካዎች ውጤታማነት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያው በምርቶች ላይ ከሚያስከትለው የዋጋ ለውጥ አንጻር ነጋዴው እያደረገው ያለው የዋጋ ጭማሪ የተጋነነ በመሆኑ ለፋብሪካዎችም ሆነ ለማህበረሰቡ ስለማይበጅ ሁሉም ሀላፊነት ተሰምቶት በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
በተለይም በገበያ ውስጥ የዋጋ ጭማሪ የሚስተዋልበት የቢራ ምርት አምራቾች ከቸርቻሪዎች ጋር በጋራ በመስራት የማስተካከል ሃላፊነት እንዳለባቸው ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡ ነገር ግን ኃላፊነታቸውን በማይወጡ አካላት ላይ መንግስት ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል ብለዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የቢዝነስ አመችነትን እየተገበረች ያለች ሀገር በመሆኗ አሁን እየተተገበረ ያለው የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ በመሆኑ አምራቾች ለሚያጋጥሟቸው ችግር በጋራ ተወያይቶ መፍትሄ እየሰጡ መሄድ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ አሁን እየታየ ላለው የዋጋ ንረትም ፋብሪካዎቹ ሀላፊነት ወስደው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል፡፡
የንግድ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እሼቴ አስፋው በበኩላቸው አዲስ የተተገበረው የኤክሳይስ ታክስ ከሌሎች ሀገሮችም ሆነ በተለያዩ ምርቶች ላይ የተጣለውን የታክስ ምጣኔ ከፍተኛ ነው ወይ የሚለውን በሚዛናዊነት መመልክት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
በአዋጁ አተገባበር ዙሪያ ግልጽነት ለመፍጠር ከሌሎች አምራቾች ጋር የሚደረጉ ውይይቶች ቀጣይነት እንደሚኖረው በውይይቱ ወቅት ተነስቷል፡፡
በመጨረሻም ለአዋጁ አተገባበር ክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር ለማድረግ ከሶስቱም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ከአምራቾች የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም ውይይቱ የተጠናቀቀ ሲሆን ለሚያጋጥሙ ችግሮች በየደረጃው የተቋቋመው ኮሚቴ በየሳምንቱና በየወሩ ተገናኝቶ መፍትሄ እንደሚየስቀምጥ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

.

Latest News

  • The permanent committee of plan, budget and finance has evaluated the four-month performance of   the Ministry of Revenues and the Customs Commission. Wed, 13 Dec 2023
The permanent committee of plan, budget and finance has evaluated the four-month performance of   the Ministry of Revenues and the Customs Commission.
  • Excise tax training  Wed, 13 Dec 2023
Excise tax training