የገቢዎች ሚኒስቴር የአስር ዓመት የብልፅግና መሪ ዕቅድ ላይ ተወያየ

 

የገቢዎች ሚኒስቴር የአስር ዓመት የብልፅግና መሪ ዕቅድ ላይ ተወያየ

የገቢዎች ሚኒስቴር የአስር ዓመት የብልፅግና መሪ ዕቅድ ላይ ተወያየ
******************************************************
ሚኒስቴር ሚስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋመቱ (ጉምሩክ ኮሚሽንና ብሔራዊ ሎተሪ) ሀገራዊ የብልፅግና ዕቅዱን እና የባለፉት ዓመታት የገቢ ዘርፉን አፈጻጸም መነሻ በማድረግ የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ማዘጋጀቱን የገቢዎች ሚኒስቴር የህግ ተገዢነት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘመዴ ተረፈ ተናግሯል።
ተቋሙ የተገልጋዮችን እርካታ በማሳደግ የመንግስትን ገቢ በብቃት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ በርካታ የአገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርም ስራዎችን እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታ ገልጸዋል። ሚኒስቴር መ/ቤቱ የብልጽግና ዕቅዱን እንደ መነሻ የወሰደው ከአገራዊ የብልጽግና ራዕይ ሲሆን ይህን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቀረፀው የአስር አመት መሪ የልማት ዕቅድ እንደመነሻ ያስቀመጠዉ ራዕይ ነው።
ይህ በእንድህ እንዳለ የአገራችን የታክስ አስተዳደር ስርዓት በኢ- መደበኛ ኢኮኖሚ፣ በህገ-ወጥ ንግድ፣ በታክስ ማጭበርበር እና በኮንትሮባንድ ምክንያት የተፈጠሩ ችግረችን በማስተካከል የመወዳደሪያ ሜዳዉን እኩል ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እንደሚሰራም ተገልጿል።
እቅዱን ለማሳካት የሚኒስቴር መ/ቤቱና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራቴኞች እንዲሁም የግብር ከፋዮቹና የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል። በተጨማሪም ዕቅዱን ለማሳካት ትኩራት የሚሹ ጉደዮች .የውስጥ እና የውጭ ስትራቴጂክ አጋርነትን ማጠናከር • ከአጋር እና ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በጋራ መንቀሳቀስ . የዳበረ የስራ ባህል ማምጣት . ግብርን በፍቃደኝነት የመክፈል ባህል ማሳደግ • ታክስ ከፋዩን በልዩ ልዩ የግንኙነት አግባቦች በማስተማር፣ በመደገፍ እና እዉቅና በመስጠት አብዛኛዉ ግብር ከፋይ በፈቃደኝነት የታክስ ግዴታውን እንዲወጣ ማስቻል • የታክስ ህግ ተገዢነት ባህሪ ለዉጥ ማምጣት ባልቻሉ አካላት ላይ ተመጣጣኝ የህግ ማስከበር ተግባር ተፈፃሚ የሚደረግበት ስርዓት ማበጀት • የታክስ እና የጉምሩክ አስተዳደር ስርዓቱን ዓለም በደረሰበት የመረጃ ቴክኖሎጂ ስርዓት እንዲደገፍ ማድረግ • የዲጂታል የገቢ አስተዳደር ስርዓት ለአገልግሎት ተቀባዩ ግልጽ፣ ቀላል እና ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት፣ የህግ ተገዥነትና አስተዳደራዊ ወጪ በመቀነስ እና የተገልጋዩን ዕርካታ በላቀ ደረጃ በማረጋገጥ የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት እንደሚሰራ ተገልጿል።

.

Latest News

  • The permanent committee of plan, budget and finance has evaluated the four-month performance of   the Ministry of Revenues and the Customs Commission. Wed, 13 Dec 2023
The permanent committee of plan, budget and finance has evaluated the four-month performance of   the Ministry of Revenues and the Customs Commission.
  • Excise tax training  Wed, 13 Dec 2023
Excise tax training