የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመዋጋት በአገር አቀፍ ደረጃ ተሻላሚ ሆኑ

የፌደራል የስራ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተመሰረበትን 20 አመት ምክንያት በማድረግ ትኩረት ለትውልድ ስነ ምግባር ግንባታ በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው አገር አቀፍ የሙስና መከላከል ሞደል ሽልማት የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመዋጋት እንዲሁም ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል የአስራር ስርዓቶችን በመዘርጋት እና አደረጃጀቶችን በመፍጠር በአገር አቀፍ ደረጃ ከፌደራል /ቤቶች አመርቂ ውጤቶችን በማምጣትና ሞዴል በመሆን በዛሬ ዕለት የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ክብርት ሳለወርቅ ዘውዴ የክልል /መስተዳደሮች፣ ሚኒስትሮች እንዲሁም ሌሎች አካላት በተገኙበት በሸራተ ሆቴል ሽልማት ተበርክቷላቸዋል፡፡

ሽልማቱን የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ በቦታው በመገኘት ከክብርት ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዛውዴ ተቀብለዋል፡፡

ሽልማቱን የሰጡት የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ውስን የሆነው የአገራችን ሀብት እንዳይባክንና ፍትሃዊነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አገልግሎት በመስጠት ህዝባችሁን በማገልገላቹ እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሰራርን በመፀየፍና ይህን ለመከላከል የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት በአገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል በመሆን በመሸለማቹን እንኳን ደስ አላቹ ብለዋል፡፡

በቀጣይም ይህን አርያአያነት ያለው ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል ህዝባንን እንደምታገልገሉም እምነቴ ነው ብለዋል፡፡ሌሎች የፌዴራል ተቋማትም የዕናንተን አርዓያነት በመከተል በየተቋማቸው ሙስናና ብልሹ አሰራርን ሊታገሉ ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፤

የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው በበኩላቸው ዕውቅናው ልናገኝ የቻልነው ለሠራተኞች፣ ለአመራሮችና ለአጋር አካላት ስልጠና በመስጠት፣ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ፣ ሀገራዊ ስሜት እንዲሰማቸው በማድረግ፣ ለሙስና በር ከፋች የሆኑ አሰራሮችን በመዝጋት፣ ስራዎችን በቴክኖሎጂ በመደገፍና ግልፅነት ባለው መልኩ መስራት በመጀመራችን ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ አልፎ በሙስና ውስጥ የተገኙትን ከስራ በማሰናበት በወንጀልም እንዲጠየቁ በማድረጋችን በአጠቃላይ ሙስናና ብልሹ አሠራርን በተደራጀ እና በተቀናጀ መልኩ መመከት በመቻላችን ይህ እውቅና ማግኘት ችለናል ብለዋል፡፡

በርካታ ለሙስና የሚያግልጡ አሠራሮች በመድፈናችንና ሠራተኛው የሀገር ተቆርቋሪነት ስሜት ኖሮት እንዲሰራ በተደረገው ጥረት በርካታ ታማኝና ሀገር ወዳድ አመራርና ሠራተኞችን ማፍራት በመቻላችን ይህን ዕውቅና አግኝተናል በዚህም ደስ ተሰኝተናል ያሉት ደግሞ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ናቸው፡፡

ይህን ዕውቅና ስናገኝ መላው የተቋማችን ሠራተኛና አመራር ከሙስናና ብልሹ አሰራር ፀድተዋል ማለት አይደለም ያሉት ሚኒስትሩ በዚህ ዕውቅና ተነሳስተን በተጀመረው መልኩ በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ ስራዎችን በመስራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንሰራለንም ብለዋል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)