ሀሰተኛ ደረሰኝ ሲታተምባቸው የነበሩ ሰላሳ አንድ ህገ-ወጥ የካሽ ሬጂስተር ማሽኖች ተያዙ

ሐምሌ 28/2013 .

በሀሰተኛ ማንነት የሀገርንና የህዝብ ሀብት ለመዝረፍ ሲውሉ የነበሩ 31 የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ የተያዙት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ነው፡፡

ደረሰኝ ግብይት መኖሩ የሚያረጋግጥ ለታክስ አሰባሰብ አገልግሎት የሚውል በመሆኑ የዕቃ ወይም የአገልግሎት ልውውጥ ሳይኖር ደረሰኝ መቁረጥ እና ማሰራጨት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 መሰረት የሚያስቀጣ ወንጀል ነው፡፡

2013 በጀት ዓመት ሚኒሰቴር መስሪያ ቤቱ በያዛቸው ህገ-ወጥ ማሽኞች ብቻ 3.2 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው ግብይት ሳይኖር ግብይት እንደተፈፀመ ተደርጎ ደረሰኝ በመቁረጥ ለታክስ ስወራ እና ማጭበርበር ውለዋል፡፡

በእነዚህ ማሽኖች ታትመው የተሰራጩ ሀሰተኛ ደረሰኞች በአንዳንድ ግብር ከፋዮች ግብርን አሳንሶ ለማሳወቅ ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ ናቸው፡፡

ሀሰተኛ ደረሰኝ አሳትሞ በማሰራጨት ወንጀል ተሳትፎ ሊኖራቸው ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ 26 ሰዎች ተይዘው ጉዳያቸው በህግ በመታየት ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ክትትል ተደርጎባቸው በግብይት ወቅት ደረሰኝ ያልቆረጡ 401 ደርጅቶች ተለይተው 20,450,000 ብር አስተዳደራዊ ቅጣት የተወሰነባቸው ሲሆን በድርጊቱ ተሳትፈዋል በሚል የተጠረጠሩ 532 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው በወንጀል እንዲጠየቁ ተደርጓል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)