የኤክሳይዝ ታክስ ፈቃድ ለመውሰድ ያላመለከታችሁ ግብር ከፋዮች በሙሉ

የካቲት 2/2013 ዓ/ም

በአዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 አንቀጽ 43(1) /እንደተሻሻለ/ የኤክሳይዝ ታክስ ፈቃድ የሌለው የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ምርቶች ማለትም በአዋጁ ሰንጠረዥ 1 ላይ የተመለከቱ ምርቶችን የሚያመርት ማንኛውም ሰው ከመጋቢት 02/2013 ዓ.ም በፊት ለታክሱ ተመዝግቦ የኤክሳይዝ ታክስ ፈቃድ ሳይዝ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ምርቶች ማምረት የማይችል በመሆኑ ከህዳር 15/2013 ዓ.ም እስከ ህዳር 30/2013 ዓ.ም ድረስ የኤክሳይዝ ታክስ ምዝገባ እንዲያመለክቱ በሚዲያ እና በተቋሙ ማህበራዊ ድህረ-ገጽ ማስታወቂያ መነገሩ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግን እስከአሁን ድረስ ለኤክሳይዝ ታክስ ምዝገባ ያላመለከቱ በርካታ ታክስ ከፋዮች ያሉ በመሆኑ እና የምዝገባ ሰርተፍኬት የሚሰጥበት ጊዜ እየተጠናቀቀ በመምጣቱ ከወዲሁ የምዝገባ ጊዜውን ማራዘም አስፈልጓል፡፡ ስለሆነም በኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ ሰንጠረዥ አንድ ላይ የተመለከቱ ዕቃዎችን የሚያመርት ማንኛውም ሰው ከመጋቢት 02/2013 በኋላ ለኤክሳይዝ ታክስ ሳይመዘገብ የሚያመርት ከሆነ በአዋጁ መሠረት አስተዳደራዊ እና የወንጀል ተጠያቂነት ያለበት መሆኑን አውቃችሁ እስከ የካቲት 10/2013 ዓ.ም ድረስ በታክስ ከፋይነት በተመዘገባችሁበት ቅ/ጽ/ቤት እየቀረባችሁ ለምዝገባ እንድታመለክቱ የገቢዎች ሚኒስቴር በጥብቅ ያሳስባል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)