የጅማ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰራተኞችና ግብር ከፋዮች ዕውቅና ሰጠ

ጥቅምት 18/2013

በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት የተሻለ የህግ ተገዢነት ባህሪ ላሳዩና ግብራቸውን በወቅቱ ለከፈሉ ግብር ከፋዮች እንዲሁም በስራ አፈፃፀማቸው ለተሻሉ ሰራተኞች በዛሬው ዕለት ዕውቅና ሰጥቷል፡፡

በእውቅና ፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የቅ/ፅ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ስመኝ ንጉሴ ይህ ዕውቅና ግብራቸውን በአግባቡና በወቅቱ ለከፈሉ እንዲሁም የተሻለ የህግ ተገዢነት ያሳዩ ሞዴል ግብር ከፋዮች የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመው ግብር ከፋዮች ሀገር የሰጠቻቸውን አደራ ተቀብለው፣ ህግና ስርዓትን አክብረው ከተገኙ ህዝብና መንግስት ሁሌም ዕውቅና እንደሚሰጧቸው አመላካች መሆኑንም ተናግረዋል ስራ አስኪያጁ፡፡ ቅ/ፅ/ቤቱ በ2012 በጀት ዓመት ለመሰብሰብ ካቀደው 1 ቢሊዮን ብር ውስጥ 801 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልፀው ይህም በአካባቢው በነበረው የፀጥታ እና የኮሮና ቫይረስ ተፅዕኖ ምክንያት እንጂ እቅዱን በተሻለ ማሳካት ይቻል እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራትም 143 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 147 ሚሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 103% ማሳካቱን ገልፀዋል፡፡ በዛሬው የዕውቅና ፕሮግራም ያልተሸለሙ ግብር ከፋዮችም ከተሸላሚ ግብር ከፋዮች ልምድ በመውሰድ በተያዘው በጀት ዓመት የተሻሉ ግብር ከፋዮች ለመሆን መጣር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ቱሉ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ተሸላሚ ግብር ከፋዮችና ሰራተኞች በ2012 በጀት ዓመት ላሳዩት ትጋት እና ታማኝነት ከምንም በላይ በራሳቸው ሊኮሩ ይገባል፡፡ በቀጣይም ቅ/ፅ/ቤቱ ላስቀመጠው የገቢ ዕቅድ መሳካት መላው ግብር ከፋይና ሰራተኛ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሊረባረቡ ይገባል ብለዋል፡፡ ለዚህም በዋነኛነት ሌብነትን መዋጋት ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የዕውቅና እና የሽልማት መርሀ ግብር ስድስት ግብር ከፋዮችና አራት ሰራተኞች ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ሽልማቱን በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ እና የታክስ ማስታወቅ ዳይሬክተር ወ/ሮ አባይነሽ አባተ የሰጡ ሲሆን በዕውቅና ስነ-ስርዓቱ ላይ ላይ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ግብር ከፋዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)