ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ (ሠንጠረዥ “ሀ”)

ከመቀጠር ሚገኝ ገቢ (ሠንጠረዥ “ሀ”) ማለት፡-

ከሠራተኛ ቅጥር ጋር በተያያዘ ሠራተኛው የተቀበለው ደመወዝ፣ ምንዳ፣ አበል፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን፣ የመልካም ስራ አፈፃፀም ማበረታቻ ስጦታ ወይም ሌላ የአገልግሎት ክፍያ እና ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም ከስራ ሲለቅ ወይም ስራ እንዲለቅ ለማግባባት የሚከፈል ገንዘብ ወይም የስራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በፈቃደኝነት፣ በስምምነት፣ በዳኝነት ውሳኔ መሠረት በጥሬ ገንዘብ (በዓይነት) የተቀበለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን እንደ ገቢ ተቆጥሮ ታክስ የሚሰላበት ይሆናል፡፡

በመቀጠር የሚገኝ ገቢ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረጉትን አይጨምርም፡፡

 

በመቀጠር በሚገኝ ገበ (ሠንጠረዥ “ሀ”) ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች

በየወሩ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ(በብር)

በየወሩ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ

ላይ ተፈፃሚ የሚሆን መጣኔ

ተቀናሽ

0-600

0%

0

601-1650

10%

600 x 10/100=60

1,651-3,200

15%

1650 x 5/100 +60= 142.5

3,201-5,250

20%

3200 x 5/100  + 142.5= 302.5

5,251-7,800

25%

5250 x 5/100  + 302.5=565

7,801-10,900

30%

7800 x 5/100  + 565= 955

10,900 በላይ

35%

10,900 x 5/100  + 955 =1,500

 

ምሳሌ

አቶ አበበ ተቀጥረው ከሚሰሩበት ድርጅት በወር 4500 ብር ይከፈላቸዋል፡፡

በመቀጥር በሚገኝ ላይ ተፈፃሚ በሚሆነው መጣኔ መሠረት የአቶ አበበ ደመወዝ ከ3201-5250 ባለው መካከል ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረት፡-

ግብር = የወር ደመወዝ  ሲባዛ የማስከፈያ መጣኔ ሲቀነስ ተቀናሽ

= 4,500x 20% -302.5

=597.50

የተጣራ ደመወዝ = አጠቃላይ ደመወዝ ሲቀነስ ተቀናሽ ግብር

= 4,500-597.50

= 3,902.5 ብር (የጡረታ ተቀናሽን ሳያካትት ከታክስ በኋላ ለሰራተኛው የሚከፈል የገንዘብ መጠን ) 

ከገቢ ግብር ነፃ የሆነ ገቢ(ሠንጠረዥ‹‹ሠ››)

ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ

በሥራ ውል መሠረት ሥራውን ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር የሚያከናውን ተቀጣሪ ለአንድ ወር ጎዞ የሚከፈለው የትራንስፖርት ወይም የነዳጅ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከጠቅላላ የወር ደሞዙ ከ1/4ኛ ባልበለጠ ብቻ ሲሆን የደመወዙ 1/4ኘኛ ከብር 2 ሺ  200 በላይ ከሆነ ታክስ ይከፈልበታል፡፡

በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል፣(ዝቅተኛው 25%፣ ለመካከለኛ 40%፣ ለከፍተኛ 60%)፤ ሲሆን የጉዳት ደረጃውን መለካት የማይቻል ከሆነ ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ ከ25% (ሃያ በአምስት መቶ) ባልበለጠ መጠን ከገቢ ግብር ነፃ ይደረጋል፡፡ በስራ ሁኔታ አስቸጋሪነት ምክንያት ለሰራተኛ የሚከፈል አበል የስራው ሁኔታ ስለሚያደርሰው ችግር ከሚመለከተው አካል ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

በስራ ቦታ አስቸጋሪነት ምክንያት ለሰራተኛ የሚከፈል አበል ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገ ሲሆን አንድ ሠራተኛ የአየር ፀባይ አበል የሚከፈለው አንደኛ ደረጃ ቆላ ከሆነ ከደመዘዉ 40 በመቶ ሁለተኛ ደረጃ 30 በመቶ እና ሶስተኛ ደረጃ 20 በመቶ አበል ከገቢ ግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው የሰቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ሲሆን ነው፡፡

አንድ ተቀጣሪ የሚከፈለው የቀን ውሎ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚያደረገው ከብር 500 ወይም ከደመወዙ 4% ካልበለጠ ብቻ ነው፡፡ አንድ ተቀጣሪ የአልጋ አበል በደረሰኝ የሚወራረድለት ከሆነ ከግብር ነፃ ሲሆን፣ ለቁረስ፣ ምሳ፣ እራትና ለመሳሰሉት 300 ብር ወይም ከደመወዙ 2.5% ሆኖ ከሁለቱ ከፍተኛ ባልበለጠ ብቻ ነው፡፡

ለማንኛውም ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ወይም ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሚከፈለው የውሎ አበል ከግብር ነፃ የሚደረገው 1000 ብር ወይም የድሞዙ 5% ከሁለቱ ከፍተኛው ባልበለጠ ብቻ ነው፡፡ ለማንኛውም ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ወይም ምክትል ሥራ አስኪያጅ የአልጋ አበል በደረሰኝ የሚወራረድለት ከሆነ ከግብር ነፃ ሲሆን፣ ቁርስ፣ ምሳ፣ እራት እና ለመሳሰሉት የሚሰጠው የውሎ አበል ከግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 600 ወይም የደመወዙ 3% ከሁለቱ ከፍተኛው ባልበለጠ ብቻ ነው፡፡

ማንኛውም የድርጅት ሥራ አስኪያጅ ወይም ምክትል ሥራ አስኪያጅ ከድርጅቱ ሥራ ጋር በተገናኝ ወደ ውጭ ሀገር ለሚያደረገው ጉዞ የሚከፈለው የውሎ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው መንግስት ከተሿሚዎቹ ውጭ ላሉት ተቀጣሪዎች በወሰነው ለውጭ አገር የውሎ አበል ልክ ላይ 20% ተጨምሮበት ይሆናል፡፡

አንድ ተቀጣሪ የተቀጠረበትን ስራ ለማከናወን ወደ ውጭ ሀገር ለሚያደረግው ጉዞ ከሚከፈለው የውሎ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው መንግስት ከተሿሚዎች ውጪ ለሌሎች ተቀጣሪዎቹ ከወሰነው የውሎ አበል ልክ ባልበለጠ ብቻ ነው፡፡

የመጓጓዣ ወጪው በቅጥር ውሉ መሠረት የተከፈለ ከሆነ ከስራ ቦታው ውጪ ተመልምሎ ለተቀጣሪ ሠራተኛ ወደ ሥራው ሲመጣ ወይም ሥራውን አጠናቆ ሲመለስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ

አንድ የውጭ አገር ዜጋ ስራውን ለማከናወን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣና የውል ዘመኑን ጨርሶ ከሀገር ሲወጣ ግብር ነፃ ሊሆን የሚችለው በተፈፀመው የቅጥር ውል መሰረት እና የአየር፣ የውሃ እና የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ዋጋ ታሪፍ መሰረት ሆኖ ከግብር ነፃ የሚከፈለው የጭነት ሂሳብ ከ300 ኪሎ ግራም ሊበልጥ አይችልም፡፡

የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ፤

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያ ሪፖብሊክ መንግስት በውጭ አገር ለሚመድባቸው ሠራተኞች የሚከፈል አበል፤

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግስት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና የክልል መንግስታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፤

ለሰራተኛው ጥቅም ተብሎ ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15%(በመቶ) ባልበለጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ፤

በመንግስት ሠራተኞች እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ

የኢትዮጵያ የፌደራል፣ የክልል ወይም የአካባቢ መንግስታት ወይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛ ሥራዎቻቸው ጋር በተያያዘ የሚያገኙት ገቢ፣

በኣለም አቀፍ ስምምነት መሰረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፣

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ መንግስት በተደረገ ስምምነት መሰረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው የሚከተሉት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ነው፡-

-ስምምነቱ የተደረገው ለመንግስት የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ ሰብአዊ ወይም አስተዳደራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሆነ እንደሆነ

-ከግብር ነፃ ማድረግ የሚያስችለውን አንቀጽ በሚመለከት ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ ሲገልጽ፤

-በማንኛውም መስክ ለላቀ የሥራ ክንውን የሚሰጥ ሽልማት፤

-በተቀባዩ ላይ በደረሰ ጉዳት ወይም በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈል ካሳ፤

-የካፒታል ሀብት በማስተላለፍ የሚገኝ ጥቅም እንደተጠበቀ ሆኖ ስጦታው የመቀጠር፣ የኪራይ ወይም የንግድ ሥራ ገቢ ካልሆነ በስተቀር በስጣታ ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤

-በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ለመከታተል የሚፈፀም ክፍያ፤

-ለቀለብ ወይም ለህፃናት ድጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፤

-ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ጋር የማይገኛን የንግድ ሥራ ገቢን ሳይጨምር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት -የሚያገኘው ገቢ፤

-ገንዘብ በሚቆጠርበት ጊዜ ለሚደርሰው ጉድለት ማካካሻ በሚሆን መጠን ብቻ ቀጣሪው ለተቀጣሪው የሚከፍለውና ለዚሁ ዓላማ መዋሉ የተረጋገጠ የጥሬ ገንዘበብ ማካካሻ ክፍያ

-በኢትዮጵያ ፀንቶ በሚሰራበት ሕግ መሰረት በተለይ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገ ገቢ፤

-ለመኖሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈል ደመወዝ፤

-በነዳጅ ሥራ ላይ የተሰማራ ሥራ ተቋራጭ ለንዑስ ሥራ ተቋራጮች የሚፈፅመው ክፍያ፡፡

-ለሠራተኛ የሚከፈል የውክልና/የኃላፊነት አበል ሥራውን የማስተዋወቅ እና የማሳደግ ላይ ለተሠማሩ ኃላፊዎች/ተቀጣሪዎች በሚቀርብ የወጪ ማስረጃ መሰረት የተከፈለ 10% ተቀናሽ ይደረጋል፤

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)