የኢትዮጵያ የቢዝነስ አመቺነት ደረጃ ለማሻሻል የሚረዱ ስራዎች ትኩረት ይሰጣቸዋል

ነሐሴ 27/2013 . (የገቢዎች /)

ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከአለማቀፍ የፋይናንስ ትብብር የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ኢትዮጵያ በቢዝነስ አመቺነት በተለይም በግብር አከፋፈል አመቺነት በአለማቀፍ ደረጃ 191 ሀገራት ያላትን 132ተኛ ደረጃ ለማሻሻል የአለም ባንክ 2020 ያወጣውን የቢዝነስ አመቺነት ሪፖርት መሰረት በማድረግ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱም ኢትዮጵያ በቢዝነስ አመቺነት በተለይም በግብር አከፋፈል አመቺነት በአለማቀፍ ደረጃ ተመራጭ እንድትሆንና አለማቀፍ ኢንቨስተሮች ወደ አገራችን በመግባት መዋዕለ ነዋያችውን እንዲያፈሱና ሰፊ የስራ እድልን በመፍጠር ወጣቱን የስራ እና የሙያ ባለቤት ለማድረግ የግብር አከፋፈል አመቺነትን ለማረጋገጥ አሳሪ የሆኑ የአሰራር ስርዓቶችን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተገልጾዋል፡፡

ታክስ ለማሳወቅ እና ለመክፈል፣ የኦዲትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ አገልግሎት ለመስጠት የሚወስደውን ጊዜ ማሻሻል የሚሉት ደግሞ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶባቸው ከሚሰሩ ስራዎች መካካል መሆናቸውን በውይይቱ ተነስቷል፡፡

የኢ-ፋይልና -ፔይመንት አገልግሎትን አሁን ከሚሰጠው አገልግሎት ይበልጥ ፈጣንና ለግብር ከፋዮች አመቺ እንዲሆን አሁን አገልግሎት እየሰጡ ካሉት አምስት ባንኮች በተጨማሪ ሌሎች ባንኮችም በስርዓቱ ቢካተቱ፣ ከኔትወርክ መቆርረጥ ጋር በተያያዘ ከቴሌ ጋር በጋራ ቢሰራ እና የተንዛዙ የክፍያ ማስታወቂያ ቅፆች ቢቀነሱ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽና የኦዲት አገልግሎትን ለማሻሻል ደግሞ የስጋት ስራ አመራርን በተጨባጭ ተግባራዊ ቢደረግ፣ የግብር ከፋዮችን ወቅታዊ የግዥ እና ሽያጭ መረጃ በተገቢው ሁኔታ ቢያዝ የሚሉ የመፍትሄ ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡ የተነሱ የመፍትሄ ሀሳቦችን ተግባራዊ ለማድረግም መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)