የገቢዎች ሚኒስቴር ከተጨማሪ ሦስት ባንኮች እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የሶስትዮሽ የአገልግሎት አሰጣጥ ስምምነት ተፈራረመ

የገቢዎች ሚኒስቴር የኤሌክትሮኒክስ የግብር ክፍያ ስርዓትን ለማስፋፋትና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት ከዓባይ ባንክ፣ ከአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ እንዲሁም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የሦስትዮሽ የአገልግሎት አሰጠጥ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል፡፡ ይህም ሚኒስቴሩ ስምምነት የተፈራረማቸውን ባንኮች ቁጥር ወደ 15 ከፍ አድርጎታል፡፡

ስምምነቱን የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት / ዓይናለም ንጉሴ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ፣ የአባይ ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ የኋላ ገሰሰ፣ የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ እና የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ ገነነ ሩጋ ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት / ዓይናለም ንጉሴ  ሀገራችን እየተጓዘችበት ያለውን የዲጂታል ትራንስፎርሚሽን መንገድ በመከተል እና አሰራራችንን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ በወረቀት ላይ የተመሰረቱ የስራ ፍሰቶችን ወደ ዲጂታል ማህደሮች የመቀየር ብሎም አገልግሎቶችን በበየነ መረብ በመታገዝ መስጠት የምንችልበትን አቅም እያጎለበትን እናገኛለን ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም ይህ የዲጂታል ገቢ አስተዳደር ስርዓት ግልፅ፣ ቀላልና ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት፣ የህግ ተገዥነትን በማሳደግና አስተዳድራዊ ወጪን በመቀነስ እንዲሁም የተገልጋዩን እርካታ በላቀ ደረጃ በማረጋገጥ የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡ ግብር ከፋዮችም ይህንን በቴክኖሎጂ የታገዘ  ስርዓት በመጠቀም ግብራቸውን  አሳውቀው እንዲከፍሉ ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ አገራችን የምትሰበስበው ገቢ በሳይበረኞች እናዳይመዘበር እና ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በኤሌክትሮኒክስ የግብር ክፍያ ስርዓት አማካኝነት ሲከፍሉ የትልልፍ ሂደቱን ደህንነት ለመጠበቅ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር  በትኩረት እንደሚስራ ገልፀዋል፡፡

የባንኮች ፕሬዘዳንቶች በበኩላቸው ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የፈፀሙትን ግብር ወደ ሚኒስቴሩ አካውንት በፍጥነት በማስተላለፍ የግብር አሰባሰብ ስርዓቱ የተቀላጠፈ እንዲሆን ለማድረግ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)