በዘጠኝ ወር ውስጥ ከ212.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
በዘጠኝ ወር ውስጥ ከ212.4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
በ2ዐ13 የበጀት ዓመት ከሐምሌ - መጋቢት 30 ባሉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 213 ቢሊዮን 85ዐ ሚሊዮን 48 ሺ 262 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 212 ቢሊዮን 473 ሚሊዮን 364 ሺ 61 ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ አፈጻጸሙም 99.36 በመቶ ሆኗል፡፡
እቅድ አፈጻጸሙ ከ2ዐ12 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የብር 29 ቢሊዮን 225 ሚሊዮን 528 ሺ 145 ወይም 15.95 በመቶ ዕድገት አለው፡፡
ገቢውም ከሀገር ውስጥ ታክስ ብር 128 ቢሊዮን 171 ሚሊዮን 912 ሺ 306፣ ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ብር 84 ቢሊዮን 135 ሚሊዮን 403ሺ 672 እንዲሁም ከሎተሪ ሽያጭ ብር 166ሚሊዮን 48ሺ 82 በድምሩ 212 ቢሊዮን 473 ሚሊዮን 364 ሺ 061 ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡
ይህ አፈጻጸም የተመዘገበው ሀገራችን በጸጥታና በኮሮና ወረርሽኝ ውስጥ ባለችበት አስቸጋሪ ወቅት በመሆኑ የተሻለ አፈጻጸም ሊባል የሚችል ነው፡፡
ለዚህ መልካም ውጤት መመዝገብ በወቅቱ ግብራቸውን የከፈሉ ግብር ከፋዮች፤ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የሌሎች አጋር አካላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም የጋራ ጥረታችንን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በብዛት የተነበቡ ዜናዎች
-
Fri, 29 Oct 2021"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
-
Wed, 4 Jan 2023"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)