ለ300 የፌዴራል ግብር ከፋዮች ለታማኝነታቸው እውቅና ተሰጣቸው

ጥቅምት 11/2014 .

የገቢዎች ሚኒስቴርግብር ለሀገሬበሚል መሪ ቃል 3 ዙር የፌዴራል ግብር ከፋዮች የዕውቅና ስነስርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የታክስ አምባሳደሮች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር / ዓብይ አህመድ በእውቅና ስነ-ስርዓቱ ላይ ለተሸላሚዎች የእንኳን ደስ አላችሁ እና የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ግብር መክፈል ሀገር የመውደድ፣ ራስን የማክበር፣ ነፃነትን የመሻት ውጤት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ግብር ከፋዮች ከታማኝነት ባሻገር ሌብነትን በመዋጋት ከመንግስት ጋር ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር አቶ ላቀ አያሌው በበኩላቸውግብር መክፈል የሀገር ፍቅር መገለጫ የሚሆነው በፍቅርና በንፅህና ሲከፈልብቻ ነው ብለዋል፡፡ ግብርን በአግባቡና በተገቢው መንገድ መክፈል ትንሹ አገራዊ መስዋዕትነት፣ የዜግነት ክብር መገለጫና ለትውልድ አሻራ ማስቀመጫ የባለቤትነት ዕድል እንጂ የግብር ከፋዩን ማህበረሰብ መቅጫና መቅረጫ ህግ አለመሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

ግብራቸውን በታማኝነት የሚከፍሉ እንዳሉ ሁሉ በግብር ስወራ የተሰማሩ፣ የሚጠበቅባቸውን ቀረጥና ታክስ ላለመክፈል ያገኙትን አጋጣሚ የሚጠቀሙ መኖራቸው የጠቆሙት አቶ ላቀ ህገ-ወጦችን ለማስተካከል የሁሉም ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሌብነት ጋር በተያያዘ ከህብረተሰቡ የሚደርሱትን ጥቆማዎች ተቀብሎ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አረጋግጥላችኋለሁ ብለዋል፡፡

.

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • 10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል Fri, 29 Oct 2021
10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል