Asset Publisher

null ‹‹የተመዘገበው ውጤት ሀገርን ያኮራ ነው›› -ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)

በአፍሪካ ምርጥ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋም ሽልማት አዘጋጅ ድርጅት (African Public Service Optimum Award) አማካኝነት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ምርጥ የአፍሪካ የጉምሩክ ኮሚሽነር በመሰኘት እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

“ምርጥ የአፍሪካ ጉምሩክ ኮሚሽነር” ሆነው እውቅና ያገኙት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በገቢዎች ሚኒስቴርና በጉምሩክ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

በአቀባበል መርሐ-ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ፤ ሽልማቱ ኮሚሽኑ ላለፉት አራት ዓመታት ከሠራተኞች ጋር በመሆን ተቋሙን ለመቀየር ባደረገው ጥረት የተመዘገበ ስኬት በመሆኑ ኮርተንባችኋል ሲሉ አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም፤ በጉምሩክ ኮሚሽን የተመዘገበውን ስኬት በቀጣይም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለመድገም በጋራ እንሠራለን ብለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን ገልጸው በአህጉር ደረጃ የተሰጠን እውቅናና ሽልማት በየደረጃው የሚገኙ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሠራተኞች ባደረጉት ጥረት ጭምር የተገኘ ውጤት ነው ብለዋል፡፡

ሽልማቱ የኢትዮጵያን ገፅታ የቀየረና ሁላችንም በተሰማራንበት ዘርፍ ጠንክረን ከሠራንና ውጤት ካስመዘገብን ወደፊት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ እንደምንል የዛሬው ሽልማት ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)