Asset Publisher

null በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ93 ቢሊየን ብር በላይ ተሰብስቧል

ከሐምሌ 1/2014 እስከ መስከረም 30/2015 ዓ.ም ወይም ባሳለፍነው ሩብ የበጀት ዓመት ከሀገር ውስጥ ታክስ እና ከወጪ ንግድና ቀረጥ 93 ቢሊየን 348.46 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ አስታወቁ፡፡
አፈጻጸሙ ከተያዘው የ95 ቢሊየን 184.36 ሚሊየን ብር ዕቅድ አንጻር የ98.07 በመቶ ክንውን ያስመዘገበ ሲሆን ይህ፤ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት 70 ቢሊየን 39.66 ሚሊየን ገቢ አኳያ በ23 ቢሊየን 308.49 ሚሊየን ብር ወይም በ33.28 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ሚኒስትሯ ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሯ አክለውም ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ የሀገር ውስጥ ገቢው ድርሻ 51 ቢሊየን 576.94 ሚሊየን ብር ሲሆን አፈጻጸሙ ከተያዘው የ50 ቢሊየን 21.64 ሚሊየን ብር ዕቅድ አንጻር የ1 ቢሊየን 555.3 ሚሊየን ብር ወይም የ103.5 በመቶ ክንውን አስመዝግቧል፡፡ ይህ፤ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት 38 ቢሊየን 762.45 ሚሊየን ገቢ አኳያ በ12 ቢሊየን 814.49 ብር ወይም በ33.06 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ብለዋል፡፡
በወጪ ንግድና ቀረጥ በኩል፤ 41 ቢሊየን 771.52 ሚሊየን ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን ከተያዘው የ45 ቢሊየን 162.72 ሚሊየን ብር እቅድ አኳያ የ92.49 በመቶ ክንውን አሳይቷል፡፡ ገቢው ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት 31 ቢሊየን 277.21 ሚሊየን አንጻር በ10 ቢሊየን 494.31 ሚሊየን ብር ወይም በ33.55 በመቶ ዕድገት እንዳለው ሚኒስትሯ አሳውቀዋል፡፡
ሚኒስትሯ ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ የሩብ ዓመቱ አፈጻጸም ሀገራችን በብዙ ፈተና ውስጥ በሆነችበት ጊዜ መመዝገቡ የተሻለ አፈጻጸም ሊያስብለው እንደሚችል እና ግብር ከፋዩንም ሆነ የግብር ሰብሳቢው ተቋም ሰራተኞች ለተገኘው ውጤት ምስጋና እንደሚገባቸው ጠቁመው በቀሪዎቹ ወራት በ2015 በጀት ዓመት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ብቻም ሳይሆን ካቀድነው በላይ ለመፈጸም ግብር ከፋዮቻችንም ሆነ የግብር ሰብሳቢው ተቋም ሰራተኞች ተቀራርበው በመስራት ለግብር አሰባሰቡ ውጤታማ መሆን ሊረባረቡ እና ሊተጉ ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)