Asset Publisher

null ለኦሮሚያ ክልል የድርቅ ተጎጂዎች ከ68 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በዛሬው ዕለት ለኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 68.7 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ባስተላለፉት መልእክት የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን እንደ ወትሮው ሁሉ የህዝብን ሃብት ለህዝብ በሚል መርህ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የተለያዩ የምግብ ነክ ቁሳቁሶች፣ አልባሳት እና ለእንስሳት መኖ ድጋፍ መደረጉን ገልጸው ችግሩን ለመፍታት በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግም ጠቅሰዋል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ስርአት ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ተስፋየ ቱሉ እና የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ /ዴኤታ ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ በርክክቡ ላይ እንደተናገሩት በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ለችግር የተዳረጉ ዜጎቻችንን ከችግሩ እስኪላቀቁ ድረስ ድጋፉን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለው ህብረተሰቡ እንዲበረታና እርስ በእርሱ ተደጋግፎ ይህንን ችግር እንዲወጣም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡትና በኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት ማእረግ የግብርና ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት አቶ አብዱራህማን አብደላ በበኩላቸው ዘንድሮ በክልሉ የተከሰተው ድርቅ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ክልሉ ባደረገው ጥሪ መሰረት ህዝባችንን ለመታደግ ሁለቱም ተቋማት እንደተለመደው ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ድጋፉ ለተጎጂዎቹ በፍትሃዊነት እንዲደርስ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችም ተጎጂዎቹ ከዚህ ችግር እስከሚወጡ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የተደረገው ድጋፍ ለአራት የክልሉ ዞኖች የሚከፋፈል እንደሆነ በርክክቡ ወቅት ተጠቁሟል፡፡

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)