Asset Publisher

null “ባለፉት ስድስት ወራት የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ14.9 በመቶ እድገት አሳይቷል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ሲሰጡ ስለታክስ እድገት የሚከተለውን ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ስድስት ወራት የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 14.9 በመቶ እድገት ማሳየቱን የተናገሩ ሲሆን አሁን ሀገራችን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ገቢው እድገት ማሳየቱ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ነገር ግን ገቢው እድገት ያሳየ ቢሆንም በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስድስት ወራት 297 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል፤ ይህም ባለፉት ስድስት ወራት ወጪ ከተደረገው 39 በመቶ እድገት አሳይቷል። በዚህም መሰረት ወጪያችን ከገቢያችን ጋር መራራቅን አምጥቷል፡፡

ወጪያችን እንደባለፉት ጊዜያት ቢሆን ኖሮ ወጪ እና ገቢያችን ይህን ያህል ልዩነት አይኖረውም ነበር ሲሉ ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመሆኑም ወጪን መቀነስ፣ ወጪን መቆጠብ እንዲሁም ሊቀሩ የሚችሉ ስራዎችን ማስቀረት እና ማዘግየት ያለብንን በማዘግየት ለገቢያችን የተቃረበ የወጪ ስርዓትን መከተል ይገባል ሲሉ አመላክተዋል፡፡

Most Viewed Assets

በብዛት የተነበቡ ዜናዎች

  • "ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው Fri, 29 Oct 2021
"ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግን በማክበርና የልዕቀት ማዕከል በመሆን አርአያ ሊሆኑ ይገባል" የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው
  • "የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Wed, 4 Jan 2023
"የሀገራችንን ኢኮኖሚ በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም በሚደረገው ጥረት የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአፍታም ቢሆን ሳናሸልብ ተግተን እንሰራለን " ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)