በታህሳስ ወር ከዕቅድ ጋር ሲነፃፀር የአንድ ቢሊዮን ብር ጭማሪ ያለው አፈፃፀም ተመዘገበ

Nested Applications

Asset Publisher

null በታህሳስ ወር ከዕቅድ ጋር ሲነፃፀር የአንድ ቢሊዮን ብር ጭማሪ ያለው አፈፃፀም ተመዘገበ

የገቢዎች ሚኒስቴር በታህሳስ ወር 21,338,652,082.91 ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 22,375,335,266.51 ብር በመሰብሰብ 105% አፈፃጸም ተመዝግቧል፡፡

በወሩ ከተሰበሰበው ገቢ 12,372,963,348.48 ብር ከሀገር ውስጥ ገቢ 9,981,796,058.96 ብር ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ እና 20,575,859.13 ብር ከሎተሪ ሽያጭ የተጣራ ገቢ የተሰበሰበ ነው፡፡

አፈፃፀሙ ከአለፈው በጀት አመት አንፃር ሲነፃፀር 4,199,868,319.15 ብር (23.11%) ዕድገት አለው።

ከዕቅድ በላይ አፈፃፀም እንዲመዘገብ አስተዋፅኦ አበርክተዋል ተብለው የተለዩ ጉዳዮች አሉ፡፡ እነዚህም ግብር ከፋዮች የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ በመክፈላቸው የሀገራዊ ገቢ አሰባሰብ ወደ ኋላ እንዳይመለስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከታቸው ነው፡፡ ይህም ታማኝ እና ሀገር ወዳድ ግብር ከፋዮች ቁጥር እያደገ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡

ዕዳ ያለባቸው ገብር ከፋዮች ዕዳቸውን እየከፈሉ መሆኑ፣ አመራና ሠራተኛው በተቀናጀ መልኩ በመስራት፣ መረጃ በመለዋወጥ፣ ተሞክሮ በመቀያየር፣ በየድርጅቱ በመገኘት ችግሮችን በመለየትና ግብር ከፋዮችን በማበረታታት፣ ድጋፍ በሚፈልጉበት ወቅት ድጋፍ በመስጠት በእረፍት ቀናት ጭምር አገልግሎት በመስጠት የግብር ከፋዮች እርካታ ለመጨመር በመሰራቱ፣ የታክስ ስርዓትን ለማዘመን ቴክኖሎጂ በተለይም የኢ-ታክስ ስርዓት፣ የአንድ መስኮት አገልግሎት፣ የጉምሩክ የወረቀት አልባ አገልግሎት በመጠቀም የገቢ አሰባሰብ ስራውን እያሳለጡ የግብር ከፋዮች ወጪና ጊዜ በመቆጠብ መስራት በመጀመራችን፣ እንደ ኢትዮ ቴሌኮም እና ባንኮች የመሳሰሉ ባለድርሻ አካላት የኢ-ታክስ አገልግሎት ተግባራዊ እንዲሆንና ግብር ከፋዮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ድጋፍ ስላደረጉልን፣ ለተሸላሚ ግብር ከፋዮች የልዩ መስኮት አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉ የሚሉ ምክንያቶች ገቢው ከዕቅድ በላይ ገቢ እንዲሰበሰብ የራሳቸው የሆነ አስተዋፅ አደርገዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው እንደገለፁት የታህሳስ ወር የገቢ ዕቅድ አፈፃፀም የተለያዩ ፈታኝ ሁኔታዎች ያልበገሩት በመሆኑ እጅግ በጣም ጥሩ የሚባል ነው። እንደሚኒስትሩ ገለፃ የገቢ አሰባሰቡን ሲፈትኑ የነበሩ ጉዳዮች ተብለው የተለዩት የኮሮና ወረርሽኝ ጫና፣ በትግራይ ክልል የጉምሩክና የሀገር ውስጥ ገቢ ሁለቱ ቅርንጫፎች ህግ ለማስከበር በተጀመረው ስራ ምክንያት ሳይሰበስቡ በመቅረታቸው፣ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ አለመረጋጋቶች ናቸው።

ከዕቅድ በላይ ገቢ እንዲሰብሰብ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸው ግብር ከፋዮች፣ የገቢዎች /ር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን እና የብሄራዊ ሎተሪ አመራሮችና ሰራተኞች እና አጋር አካላት ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Asset Publisher

ዜና

  • የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ Fri, 29 Mar 2024
የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
  • በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል Mon, 18 Mar 2024
በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል
  • የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ Fri, 15 Mar 2024
የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

Nested Applications

Asset Publisher

.