ለራስ እና ለቃል መታመን

Nested Applications

Asset Publisher

null ለራስ እና ለቃል መታመን

ህዳር 24 2016 . (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ተራማጅ አስተሳሰብን በማጎልበት ሙስናን መታገል እንደሚገባ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የጸረ-ሙስና ቀንን በጋራ ባከበሩበት ወቅት ነው።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር / አይናለም ንጉሴ የገቢውን ዘርፍ እንዲመራ ኃላፊነት የተሰጠው ሚኒስቴር /ቤቱ በቀጣይ ዓመታት ሃገራዊ ወጪ በሀገር ውስጥ ገቢ እንዲሸፈን በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረው ይህ ዓላማ ሊሳካ የሚችለው ከሙስና እና ከብልሹ ተግባር የጸዳ አሰራር ተግባራዊ ሲደረግ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም ለራሳችን እና ለቃላችን ታምነን ስራችንን መስራት አለብን ብለዋል።

ሚኒስትሯ በተጨማሪም በተቋሙ ሙስናን ቀድሞ የመከላከል ስራ በመከናወን ላይ እንዳለም ጠቅሰው በቀጣይም ይሄው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።

ሌላው በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የፌዴራል ጸረ-ሙስና እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን /ኮሚሽነር አቶ አሸቴ አስፋው መንግስት በሀገር ደረጃ እየተስተዋለ ያለውን የሙስና ችግር ለመቅረፍ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነው ብለዋል የገቢዎች ሚኒስቴርም ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እያከነወናቸው ያሉት ተግባራት አበረታች ናቸው ያሉ ሲሆን በቀጣይም ተግባራቱ ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

በመድረኩ የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የጉምሩክ ምክትል ኮሚሽነሮች እና የተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን በፌዴራል ጸረ- ሙስና እና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን የተዘጋጀ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

Asset Publisher

ዜና

  • ማስታወቂያ Sat, 18 May 2024
ማስታወቂያ
  • የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ Fri, 29 Mar 2024
የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
  • በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል Mon, 18 Mar 2024
በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

Nested Applications

Asset Publisher

.