የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ተሾሞለታል (ነሐሴ 13/2014 ዓ.ም)

Nested Applications

Asset Publisher

null የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ተሾሞለታል (ነሐሴ 13/2014 ዓ.ም)

ነሐሴ 13/2014 ዓ.ም

የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት ክቡር አቶ ላቀ አያሌው በትምህርት ምክንያት ወደውጪ ሀገር ለመሄድ በሚኒስተሮች ምክር ቤት መሸኘታቸውን ተከትሎ ሚኒስቴሩ አዲስ ሚኒስትር ተሾሞለታል፡፡ (ነሐሴ 13/2014 ዓ.ም)

በዚህም መሰረት በወሎ ዩንቨርሲቲ ምክትል ፕሬዘዳንትነት፣ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው የሰሩት እና በአማራ ክልል በኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪነት ይሰሩ የነበሩት ክብርት / ዓይንዓለም ንጉሴ የገቢዎች ሚኒስትር በመሆን የተሾሙ ሲሆን በዛሬው እለት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የስራ ርክክብ እና የሽኝት ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡ 

የኃላፊነት ርክክብ በተደረገበት ወቅት ክቡር አቶ ላቀ አያሌው ባስተላለፉት መልእክት የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በቆይታቸው ስራቸውን እና ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ላገዟቸው ለገቢዎች ሚኒስትር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተደራጀና ሥራቸውን በእውቀት የሚሰሩ የሕዝብ አገልጋዮች የሚገኙበት ከመሆኑም በተጨማሪ በቆይታቸው ለተደረገላቸው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና እና ክብር እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ ከዚሁ ጋር አያይዘውም ከሰባት ወራት በፊት ለመንግሥት ባቀረብኩት የሥራ መልቀቂያ መሰረት ለአገርና ለሕዝብ ከዚህ የበለጠ ለማገልገል አቅም እንዳገኝ ውጭ አገር የመማር ፈቃድ ስለተሰጠኝ አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡

ክቡር አቶ ላቀ በተጨማሪም 2022 ሀገራችን የራሷን ወጪ በራሷ ገቢ ለመሸፈን የያዘችውን ራእይ ለመሳካት እንዲሁም 2015 በጀት ዓመት ተቋሙ 450 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ያቀደውን በብቃት እንዲፈጽም ከፍተኛ የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች ከአዲሷ ሚኒስቴር ጎን በመሆን ስራቸውን በኃላፊነት እና በቅንነት መስራት ይጠበቅባችኋል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በተቋሙ በሚኒስትርነት የተሾሙት ክብርት / አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው ተቋሙ ጠንካራ አደረጃጀት እና የአሰራር ስርዓት ያለው፤ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸሙም በየጊዜው እድገት እያስመዘገበ የሚገኝ እንደመሆኑ ይህንኑ ስኬት ማስቀጠል ብቻ ሳይሆን 2015 በጀት ዓመት ለመሰብሰብ ከታቀደው በላይ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እንዲሁም ሀገራችን እና ህዝባችን የሚጠብቅብንን ለመወጣትም ሁሉም የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች ከጎናቸው በመሆን በጋራ እና በትልቅ የኃላፊነት መንፈስ የልማት ወጪን በራሷ መሸፈን የምትችል ሀገር እንድትኖረን ለሚደረገውን ጥረት መረባረብ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡    

Asset Publisher

ዜና

  • በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል Mon, 18 Mar 2024
በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል
  • የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ Fri, 15 Mar 2024
የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ
  • የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት Thu, 29 Feb 2024
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

"ውጤታማነት በጅማ"

Nested Applications

Asset Publisher

.