ከ41 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የገቢ ትልልፍ ተደርጓል -ክብርት ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)

Nested Applications

Asset Publisher

null ከ41 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የገቢ ትልልፍ ተደርጓል -ክብርት ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)

የፌዴራል፣ የክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የገቢ ዘርፍ ተቋማት የጋራ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

የፌዴራል፣ የክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የገቢ ዘርፍ ተቋማት 2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና 2015 በጀት ዓመት እቅድ የጋራ ውይይት መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር / አይናለም ንጉሴ 2014 በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ 497.45 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 481.71 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልጸው 2015 በጀት ዓመትም በሀገር አቀፍ ደረጃ 646.75 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ እቅድ ተይዟል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም የገቢዎች ሚኒስቴር የፌደራል እና የክልል መንግስታትን የጋራ ገቢን እና በውክልና የሚሰበሰቡ ታክሶችን ሰብስቦ ለክልሎች የሚያስተላልፍ መሆኑን አንስተው 2014 በጀት ዓመት 34.69 ቢሊዮን የጋራ ገቢ እና 6.325 ቢሊዮን የውክልና ታክሶችን በመሰብሰብ በጥቅሉ 41.02 ቢሊዮን ለክልሎች ማስተላለፉን አንስተዋል:: 

2014 በጀት ዓመት እቅድ ክንውን እና 2015 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ በተጨማሪ የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና የሞጁላር ስልጠና ምንነት እና ጠቀሜታ ላይ፣ የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አፈታት በተመለከተ እና የተገልጋዮች ቻርተር ዝግጅት እና ትግበራ የተመለከተ የልምድ ልውውጥ እና ውይይት በቀጣይ ከመድረኩ የሚጠበቁ የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች መሆናቸውን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል፡፡   

Asset Publisher

Asset Publisher

ዜና

  • የጉምሩክ ኮሚሽን ያከናወናቸው የለውጥ ተግባራት ለሌሎች ሴክተር መ/ቤቶች ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Fri, 23 Sep 2022
የጉምሩክ ኮሚሽን ያከናወናቸው የለውጥ ተግባራት ለሌሎች ሴክተር መ/ቤቶች ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)
  • ከ41 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የገቢ ትልልፍ ተደርጓል -ክብርት ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር) Fri, 23 Sep 2022
ከ41 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የገቢ ትልልፍ ተደርጓል -ክብርት ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)
  • የገቢዎች ሚኒስቴር ከተጨማሪ ሦስት ባንኮች እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የሶስትዮሽ የአገልግሎት አሰጣጥ ስምምነት ተፈራረመ Fri, 23 Sep 2022
የገቢዎች ሚኒስቴር ከተጨማሪ ሦስት ባንኮች እና ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የሶስትዮሽ የአገልግሎት አሰጣጥ ስምምነት ተፈራረመ

የኤሌክትሮኒክስ ታክስ የማስታወቂያ ዘዴ /E-tax/ ማሻሻያ የተደረገባቸው የታክስ ማስታወቂያ ቅፆች

Asset Publisher

Nested Applications

Asset Publisher

.