ራሳችንና የምንመራቸውን ድርጅቶች ከገቢ አሰባሰብ እንከኖች ነጻ በማድረግ ለታክስ ሕግ ተገዥ የሆነ ህብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል -(የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ )

Nested Applications

Asset Publisher

null ራሳችንና የምንመራቸውን ድርጅቶች ከገቢ አሰባሰብ እንከኖች ነጻ በማድረግ ለታክስ ሕግ ተገዥ የሆነ ህብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል -(የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ )

በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት በገቢ አሰባሰብ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማረም እና ለማስተካከል የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከግብር ከፋዮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የገቢዎች ሚኒስትር / አይናለም ንጉሴ  ራሳችንና የምንመራቸውን ድርጅቶች ከገቢ አሰባሰብ እንከኖች ነጻ በማድረግ ለታክስ ሕግ ተገዥ የሆነ ህብረተሰብ ለመፍጠር ያለሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል ያሉ ሲሆን ከፍተኛ ግብር ከፋዮቻችን የሚጠበቀውን የገቢ ድርሻችሁን ለመወጣት እና ለሀገራችን ልማት እና ብልጽግና ከፍተኛ ድርሻ ያለውን ገቢ በአዲሱ ዓመት በተሻለ ሁኔታ ለመሰብሰብ እጅ ለእጅ ተያይዘን እና ተደጋግፈን ለበለጠ ስኬት መረባረብ ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በታክስ ዘመኑ ለመሰብሰብ የታቀደው አመታዊ የገቢ እቅድ በገቢዎች ሚኒስቴር እና በተዋረድ ባሉ ተቋሞቻችን ይታቀድ እንጂ የዚህ እቅድና የቀጣይ ተግባር ባለቤቶች እናተ ግብር ከፋዮች በመሆናችሁ የታቀደውን ለማሳካት ብቻ ሳይሆን ለተጨማሪ ውጤት በመስራት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአስተማማኝ መሰረት ላይ እንዲገነባ በማደረግ እና የተከበረች ሀገር በመገንባት ሂደት ውስጥ ያልተቆጠበ ሚናችሁን በመወጣት የከበረች ሀገር ዜጎች እንድንሆን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የከፍተኛ ግብር ከፋዮች //ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ተሬሳ እንሴሱ //ቤቱ 2014 በጀት ዓመት 136.6 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን እና 2015 በጀት ዓመትም 183.9  ቢሊዮን ገቢ ለመሰብሰብ እቅድ መያዙን እና ለዚህም ስኬት ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ግብር ከፋዮችም ከባንክ ዋስትና፣ ከተቀናሽ ወጪ አያያዝ እና ከተመላሽ እንዲሁም ከደረሰኝ ጋር ተያይዞ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን አንስተው የችግሩን ምንጭ እና መፍትሄያቸውን በተመለከተ የተለያዩ የስራ ክፍሎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተውበታል፡፡

Asset Publisher

ዜና

  • የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ Fri, 29 Mar 2024
የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
  • በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል Mon, 18 Mar 2024
በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል
  • የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ Fri, 15 Mar 2024
የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

"ውጤታማነት በጅማ"

Nested Applications

Asset Publisher

.