ዛሬ የገጠመንን ፈተና ልክ እንደ አድዋ ድል ሁሉ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥረትና ህብረት መቀልበስ ይገባል - አቶ ላቀ አያሌው የገቢዎች ሚኒስትር

Nested Applications

Asset Publisher

null ዛሬ የገጠመንን ፈተና ልክ እንደ አድዋ ድል ሁሉ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥረትና ህብረት መቀልበስ ይገባል - አቶ ላቀ አያሌው የገቢዎች ሚኒስትር

የገቢዎች ሚኒስቴር ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመሆን በሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች 31 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

በድጋፍ አሰጣጥ መርሀግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ምክትል / እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ባደረጉት ንግግር ሀገራችን በአሁኑ ወቅት በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ሳቢያ ከፍተኛ የዜጎች መፈናቀልን እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ በተለይም በሶማሌ //መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያጋጠመው ድርቅ የሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ድጋፍና ርብርብ የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ሚኒስቴር /ቤቶችም አሰፈላጊውን ሁሉ ያደርጋሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው በበኩላቸው ሚኒስቴር /ቤቱ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመሆን በሀገራችን የተለያዩ አካባዎች በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለመደገፍ ተከታታይ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል፡፡ አሁን የገጠምንን ፈተና እንደ አድዋ ድላችን ሁሉ በተባበረ የኢትዮጵያውያን ጥረት ማልፍ ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ሚኒስቴር /ቤቱ ከጉምሩክ ኮሚሽንና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ከችግሩ አንፃር የተበረከተው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነ ጠቅሰው ተጨማሪ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ክልሉ በዚህ ዓመት ያጋጠመው ድርቅ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ነው ብለዋል፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ክልሉ ከገጠመው ችግር በቶሎ እንዲወጣ ላደረጉት ሁለገብ አስተዋፅኦ በክልሉ ህዝብ እና መንግስት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በዛሬው ዕለት የተደረገው ድጋፍ የእንስሳት መኖ፣ ዱቄት፣ ምግብ ነክ ቁሳቁሶች፣ አልባሳትና 5 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በድጋፍ አሰጣጥ መርሀ ግበሩ ላይ የተለያዩ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችተገኝተዋል

Asset Publisher

ዜና

  • የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ Fri, 29 Mar 2024
የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በዛሬው ዕለት የስምምነት መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
  • በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል Mon, 18 Mar 2024
በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል
  • የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ Fri, 15 Mar 2024
የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

"ውጤታማነት በጅማ"

Nested Applications

Asset Publisher

.