10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል

Nested Applications

Asset Publisher

በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል

በሪፎርም ስራዎች እና በታክስ ሕግ-ተገዥነት ላይ የምክክር መድረክ ተካሂዷል Mon, 18 Mar 2024

የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ

የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የውይይት መድረክ Fri, 15 Mar 2024

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት Thu, 29 Feb 2024

የገቢዎች ሚኒስቴር ጽ/ቤት እና ተጠሪ የመ/ቤቱ ዳሪክቶሬቶች የስድሰት ወር የሰራ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ

የገቢዎች ሚኒስቴር ጽ/ቤት እና ተጠሪ የመ/ቤቱ ዳሪክቶሬቶች የስድሰት ወር የሰራ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ Fri, 26 Jan 2024

Asset Publisher

null 10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት ተችሏል

እስካሁን በተሰራ ስራ 10 ሺህ ተጠቃሚዎች ወደ አንድ መሰኮት አገልግሎት ስርዓት ማስገባት መቻሉን የአንድ መስኮት የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ተስፋዬ ለተጠቃሚዎች ስልጠና በተሠጠበቅ ወቅት ገልፀዋል፡፡ ስልጠናን ጨምሮ በቪዲዮ የታገዘ መረጃዎችን በማሰራጨት ተጠቃሚዎችን ከአገልግሎቱ ጋር የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክስ አንድ መስኮት አገልግሎት ያደጉ ሀገራትና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የንግድ ተወዳዳሪነትን ከፍ ለማድረግ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው፡፡

በኢትዮጵያም 16 የመንግስትና የግል መስሪያ ቤቶች የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክስ አንድ መስኮት አገልግሎትን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡

የአገሪቱን የገቢና ወጪ አገልግሎት ግልፅነት የጎደለው፣ ለሙስና እና ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ እንዲሁም አገልግሎቱን ለማገኘት በርካታ ጊዜ ይጠፋ እንደነበር ያነሱት አቶ ሮቤል ተስፋየ የኤሌክትሮኒክስ አንድ መስኮት አገልግሎት እነዚህንና መሰል ችግሮች በመፍታት በኩል የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣዮቹ ስድስት ወራት እስከ 3 ሰልጣኞች ከአገልግሎቱ ጋር የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራ ነው የገለፁት፡፡

የአንድ መስኮት አገልግሎትን ቀደም ሲል እየተጠቀሙበት እንደሚገኙና ጊዜና ገንዘባቸውን ከአላስፈላጊ ወጭ እንዳዳነላቸው አስተያየታቸውን የሰጡን ሰልጣኞች የገለፁ ሲሆን ስልጠናው በአጠቃቀም ወቅት ይገጥማቸው የነበረውን ችግር እንደሚቀርፍላቸው አንስተዋል፡፡

Asset Publisher

Untitled Basic Web Content

"ውጤታማነት በጅማ"

Nested Applications

Asset Publisher

.