ለተቀላጠፈ አገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላትዎን ያረጋግጡ
ዜና
የገቢዎች ሚኒስቴር በኤሌክትሮኒክስ የስራ ግብር ለማስታወቅና ለመክፈል (e-filing and e-payment) ለተቀጣሪዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጠው፡-
ከ50 በላይ ተቀጣሪ ላላቸው ድርጅቶች የሰራተኞችን ዝርዝር የያዘ ደብዳቤ ለዋና መስሪያ ቤት ሲቀርብ የመ/ቤቱ ባለሙያዎች በየድርጅቱ በመገኘት መረጃ ይሰበስባሉ
የውጭ ሀገራት ዜጎች ሆነው የመኖሪያና የስራ ፍቃድ ለያዙ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵዊ ሆነው በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ዜጎች ቢጫ ካርድ ወይም ፓስፖርት ማቅረብ ይኖርባቸዋል
በውጭ ሀገራት የሚገኙ ዜጎች የቲን ምዝገባ መረጃ የተወሰደበትን የግል መረጃ መሙያ ቅጽ : የአሻራ መረጃ የተወሰደበት ቅጽ እና የመኖሪያ ፈቃድ(ፓስፖርት) ኮፒ እንዲሁም የውክልና ደብዳቤ ማስረጃዎች ይዘው ለሚቀርቡ ተገልጋዮች:
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የጠፋባቸውና ሲስተም ላይ እንዲታይላቸው ለሚፈልጉ ተገልጋዮች:
በአደጋ ወይም ሌላ የተፈጥሮ ችግር ምክንያት የጣት አሻራ መረጃ በየክፍለ ከተማ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤቶች መስጠት ያልቻሉ ባለጉዳዮች የድጋፍ ደብዳቤ እና የታደሰ መታወቂያ ይዘው ሲቀርቡ አገልገሎት ማግኘት ይችላሉ::
ነገር ግን ቁጥራቸው ከ50 በታች የሆነ አገልግሎት ፈላጊ የነዋሪነት መታወቂያ እና ከሚሰሩበት መ/ቤት የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ በመያዝ መ/ቤታቸው በሚገኝበት የክፍለ ከተማ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመቅረብ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡