የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች አምራቾች በሙሉ
ዜና
በአገር ውስጥ በሚመረቱ ምርቶች ወይም ወደ አገር በሚገቡ እና የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው ዕቃዎች ላይ ተፈጻሚ የሚሆን አዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 1186/2012 ወጥቶ ከየካቲት 06/2012 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ መዋሉ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም በአዋጁ መሰረት የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ምርቶች የሚያመርት ማንኛውም ሰው ከመጋቢት 2/2013 ዓ.ም በፊት ለታክሱ ተመዝግቦ የኤክሳይዝ ታክስ ፈቃድ ያልያዘ እንደሆነ ከመጋቢት 2/2013 ዓ.ም በኋላ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ምርቶች ማምረት የማይችል በመሆኑ ለኤክሳይዝ ታክስ ምዝገባ እና የኤክሳይዝ ታክስ ፈቃድ ለማውጣት በኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ እና ማስፈጸሚያ መመሪያ ቁጥር 67/2013 መሠረት መሟላት የሚገባቸውን ቅድመ-ሁኔታዎች በማሟላት በግብር ከፋይነት ከተመዘገባችሁበት የታክስ ማዕከል ወይም ከታክስ ባለስልጣኑ ድህረ-ገጽ ወይም መገናኛ ከሚገኘው የዋናው መ/ቤት የኤክሳይዝ ታክስ አስተግባሪ ግብረ-ኃይል የስራ ክፍል የምዝገባ ማመልከቻ ፎርም በመወሰድ የምዝገባ ማመልከቻ ቅጹን በአግባቡ ሞልታችሁ እስከ ህዳር 30/2013 ዓ.ም ድረስ ለታክስ ማዕከላችሁ ለምዝገባ እንድታመለክቱ እናሳስባለን፡፡
"ውጤታማነት በጅማ"