የአራተኛው ዙር የፌዴራል ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ሥነ-ስርዓት ላይ እውቅና እና ሽልማት ያገኙ ግብር ከፋዮች ዝርዝር
በእውቅና እና ሽልማት መርሐ-ግብሩ 400 ታማኝ ግብር ከፋዮች የተሸለሙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 40 የሚሆኑት የፕላቲኒየም፣ 120 የወርቅ እና 240 ደግሞ የብር ተሸላሚዎች ሆነዋል። 14 ግብር ከፋዮች ደግሞ ለሦስት ተከታታይ ጊዜ እና ከዛ በላይ ተሸላሚ በመሆን ልዩ ተሸላዎች ሲሆኑ አንድ ግብር ከፋይ ሙስናና ብልሹ አሰራርን በማጋለጥ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በሀገር ውስጥ ታክስ መሰረታዊ የግብር ከፋይ መረጃ፣ ታክስ ማሳወቅ፣ የግብር ከፋዩ የቅጣት ታሪክ፣ የኦዲት ግኝት ልዩነት፣ የግብር/ታክስ ስሌት ልዩነት እና ሌሎች በድምሩ 12 የሚሆኑ መስፈርቶች እንዲሁም በጉምሩክ ኮሚሽን ደግሞ የገቢ አስተዋጽኦ፣ የሕግ ተግዥነት፣ ወቅታዊ የስጋት ፕሮፋይል፣ የህግ ተገዥነት ታሪክ እና የጉምሩክ ጥፋት ዓይነት የሚሉ ደግሞ ታማኝ ግብር ከፋዮችን ለመመረጥ ጥቅም ላይ የዋሉ መስፈርቶች ናቸው፡፡
















