ያልተፈቀዱ ወይም ተቀናሽ የማይደረጉ ወጪዎች

Posted in Know How

ያልተፈቀዱ ወይም ተቀናሽ የማይደረጉ ወጪዎች

ያልተፈቀዱ ወጪዎች ታክስ ከፋዮች በህግ እንደ ወጪ እንዳይያዝላቸው የተከለከለ ወጪ ሲሆን ታክስ ከፋዮች እነኚህን ወጪ ቢያወጡ እንኳ በታክስ ህግ የተከለከለ በመሆኑ ሚኒስቴር /ቤቱ ውድቅ ያደርጋቸዋል፡፡

በፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀፅ 27 መሰረት ተቀናሽ የማይደረጉ ወጪዎች በግልፅ የተመለከቱ ሲሆን ለመጥቀስ ያክል፣

  • በጥፋት ምክንያት የተከፈለ የጉዳት ካሳና መቀጫ፣
  • የግል ፍጆታ ወጪዎች፣
  • የመድን ዋስትና ሽፋን ያለው ጉዳትና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

እነዚህ ወጪዎች በአንድ በኩል በመሰረታዊ የሂሳብ መርሆ የተፈቀዱ ሊሆኑ የሚችሉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ታክስ ከፋዮች ለገቢዎች ሚኒስቴር የሚያቀርቡት ተጨማሪ ገቢ ለማግኘትና ለንግድ እንቅስቃሴያቸው ዋስትና ለመስጠት የወጣ ወጪ ነው በሚል ነው፡፡

Visitors: Yesterday 38 | This week 229 | This month 285 | Total 431139

We have 275 guests and no members online