የውሎ አበል

Posted in Know How

የውሎ አበል ማለት አንድ ተቀጣሪ የተቀጠረበትን ሥራ ለማከናወን መደበኛ የስራ ቦታው ከሚገኝበት ከተማ ውጪ ከ25 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ በሚሄድበት ጊዜ ለመኝታ ፣ለምግብ ፣ለመጠጥና ለተዛማጅ ወጪዎች የሚከፈል አበል ነው፡፡

የውሎ አበል ከግብር ነፃ የሚደረግበት ሁኔታ
1.በሀገር ውስጥ ለሚደረጉ ጉዞች የሚከፈል ውሎ አበል፤
ሀ.አንድ ተቀጣሪ የሚከፈለው ቀን ውሎ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 500 ወይም ከደሞዙ 4% ከሁለቱ ከፍተኛ ከሆነው መጠን ባልበለጠ ብቻ ነው፡፡

ለ. ለፊደል ተራ ሀ አፈፃፀም አንድ ተቀጣሪ የአልጋ አበል ያለገደብ ወይም በተወሰነ ገደብ በደረሰኝ የሚወራረድለት ከሆነ በደረሰኝ መሰረት ለአልጋ የተከፈለው ገንዘብ ከግብር ነፃ የሚደረግ ሲሆን ለቁርስ ፣ ምሳ፣ እራት የመሳሰሉ ወጪዎች የሚሰጠው የውሎ አበል ከግብር ነፃ ሊደርግ የሚችለው ከብር 300 ወይም ከደሞዙ 2.5 % ከሁለቱ ከፍተኛ ከሆነው መጠን ባልበለጠ ብቻ ነው፡፡

ሐ.ለማንኛቸውም ድጅት ስራ አስኪያጅ ወይም ምክትል ስራ አስኪያጅ የሚከፈለው የውሎ አበል ከግር ነፃ የሚደረገው ከብር 1000 ወይም ከወርሓዊ ደሞዙ 5 በመቶ ከፍተኛ ከሆነው መጠን ባልበለጠ ብቻ ነው ፡፡

መ.ለፊደል ተራ ሐ አፈፃፀም አንድ ስራ አስኪያጅ ወይም ምትል ስራ አስኪያጅ የአልጋ አበል ያለገደብ ወይም በተወሰነ ገደብ በደረሰኝ የሚወራረድለት ከሆነ በደረሰኙ መሠረት ለአልጋ የተከፈለው ገንዘብ ከግብር ነፃ የሚደረግ ሲሆን ፣ ለቁርስ ምሳ፣ እራ እና ለመሳሰሉ ወጪዎች የሚሰጠው የውሎ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው ከብር 600 ወይም ከወርሓዊ ደሞዙ 3 በመቶ ከፍተኛ መጠን ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡
2.ወደ ውጪ ሀገር ለሚደረጉ ጉዞዎች የሚከፈል የውሎ አበል ፣
ሀ.አንድ ተቀጣሪ የተቀጠረበትን ስራ ለማከናወን ወደ ውጪ ሀገር ለሚያደርገው ጉዞ የሚከፈለው የውሎ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚደረገው መንግስት ከተሿሚዎች ወጪ ለሌሎች ተቀጣሪዎች ከወሰነው የውሎ አበል ልክ ባልበለጠ ብቻ ነው፡፡
ለ.የማናቸውም ድርጅት ስራ አስኪያጅ ወይም ምክትል ስራ አስኪያጅ ከድርጅቱ ስራ ጋ በተገናኘ ወደ ውጪ ሀገር ለሚያደርገው ጉዞ የሚከፈለው የውሎ አበል ከገቢ ግብር ነፃ የሚያደርገው መንግስት ከተሿሚዎች ውጪ ለሌሎች ተቀጣሪዎች በወሰነው የውሎ አበል ልክ ላይ 20 በመቶ ተጨምሮበት ይሆናል፡፡
3.ለተራ ቁጥር 2 ድንጋጌ ቢኖርም በሀገር ውስጥ ለሚደረግ የስራ እንቅስቃሴ የኮንስትክሽን ማሽነሪ ኦፕሬተሮች የሚከፈል የውሎ አበል ከ25 ኪ.ሜ ባነሰ ወይም በበለጠ ርቀት ቢሆንም የተከፈለው የውሎ አበል ከግብር ነፃ ይሆናል፡፡
4.በተራ ቁጥር 2 እና 3 የተገለፀው ቢኖርም የመንግስት መስሪያ ቤት ለተሿሚዎች እና ለተቀጣሪዎቻቸው ከመደበኛ የስራ ቦታቸው ውጪ ከ25 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀው በመሄድ ለሚያከናውኑት ስራ የሚከፍሉት የቀን ውሎ አበል ሙሉ በሙሉ ከግብር ነፃ ተድርጓል፡፡

 

Visitors: Yesterday 38 | This week 229 | This month 285 | Total 431139

We have 287 guests and no members online