ኤክሳይዝ ታክሰ

Posted in Know How

ኤክሳይዝ ታክስ የቅንጦት እቃዎች ሆነው ዋጋቸው ጨመረም አልጨመረም መሰረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ፣ እንዲሁም የሕብረተሰቡን ጤንነት የሚጎዱና ማህበራዊ ችግር የሚያስከትሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም ለመቀነስ ሲባል የሚጣልታክስ ሲሆንማህበራዊ ጠቀሜታ የሌላቸው እና የህብረተሰቡን ጤንነት የሚጎዱ ምርቶች መቀነስ እንዲሁም የቅንጦት የሆኑ የፍጆታ እቃዎች ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ነው፡፡ የተሻለ ገቢ ያላቸው ሠዎች በሚጠቀሙባቸው እቃዎች እና የመግዛት ፍላጎታቸው በማይቀንስባቸው ምርቶች ላይ ታክሱ ይጣላል፤ ምክንያቱም ለአገር ተጨማሪ ገቢ ያስገኛልና፡፡

እንዴት ይሰላል

ታክሱ የሚሰላበት ዋጋ /ስሌት/ ዕቃዎቹ በሀገር ውስጥ የተመረቱ ከሆነ የማምረቻ ወጪው ይሆናል፡፡ ይህም ማለት ምርቱ ሲመረት በቀጥታ ለምርቱ ተግባር የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎችና የጉልበት ዋጋ፣ ቀጥተኛ ያልሆኑ ግብዓቶች/overhead costs/ እና ተጨማሪ ወጪዎች ናቸው፡፡ ስሌቱ የማምረቻ መሳሪያዎችን እርጅና እና ቅናሽ ታሳቢ አያደርግም፡፡ እንዲሁም ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ከሆነ ታክሱ የሚሰላው የዕቃው የግዥ ዋጋ / cost of goods/፣ የመድህን አረቦን/Insurance/ እና የመጓጓዣ ወጪዎች እንዲሁም የጉምሩክ ቀረጥ ናቸው፡፡

በኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 570/2000 አንቀፅ 2 ድንጋጌ መሰረት በፋብሪካ ከጨርቃ ጨርቅ የሚሰሩ ወይም የሚዘጋጁ ልብሶች አገር ውስጥ ሲመረቱ እና ተሽከርካሪዎች አገር ውስጥ ሲገጣጠሙ ሊከፈል የሚገባው ኤክሳይዝ ታክስ በሚሰላበት ጊዜ ለእነዚህ ዕቃዎች ማምረቻ የዋሉ ግብዓቶች ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ የተከፈለው ኤክሳይዝ ታክስ ተቀናሽ ይሆናል፡፡         

የመክፈያጊዜው

ዕቃዎች የተመረቱት በሀገር ውስጥ ከሆነ ከተመረቱበት ወር ቀጥሎ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ፤ ዕቃዎቹ ከውጪ ሲገቡ ደግሞ አስመጪው ግለሰብ ወይም ድርጅት ከጉምሩክ ክልል በሚያወጣበት ጊዜ ታክሱ ይከፈላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ዕቃዎቹን ያመረተው ግለሰብ ወይም ድርጅት የታክስ ባለስልጣኑ በሚፈቅድለት የዕቃ መጋዘን ውስጥ ታክስ ሳይከፍል እንዲቀመጥለት ፈቃድ ከጠየቀና ባለስልጣኑም ከፈቀደ ለዕቃዎቹ ታክስ የሚከፈለው ከመጋዘን ሲወጡ ይሆናል፡፡

Visitors: Yesterday 38 | This week 229 | This month 285 | Total 431139

We have 245 guests and no members online