ስለ ተጨማሪ እሴት ታክስ በጥቂቱ

Posted in Know How

ግብር/ታክስ ማለት በመዝገበ ቃላት ፍቺው በህግና ደንብ ላይ ተመርኩዞ መንግስት ከህዝብና ከድርጅቶች ላይ ገቢ የሚያገኝበት ስልት ነው፡፡ በመሆኑም መንግስት የህዝቡን ሁለገብ ጥያቄዎች ይፈታ ዘንድ የበጀት ምንጩ ግብር/ታክስ ነው፡፡

ግብር/ታክስ ቀጥተኛ፣ ቀጥተኛ ያልሆኑና ሌሎች ተብሎ በሶስት ምድብ ይከፈላል፡፡ ቀጥተኛው፤ ከመቀጠር ፣ ከቤት ኪራይ እና ከንግድ ስራ የሚገኝ ገቢ ግብርን ሲያጠቃልል፤ ቀጥተኛ ያልሆኑት በሚለው ምድብ ውስጥ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ተርን ኦቨር ታክስ፣ ኤክሳይዝ ታክሰ፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ የቴምብር ቀረጥ እና ሱር ታክስ ተካተዋል፡፡ ከእነዚህ ውጭ ያሉት “ሌሎች” ተብለው ተፈርጀዋል፡፡  በዚህ ጽሑፍ ስለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ጥቂት ብለናል፤ መልካም ንባብ፡፡

ተጨማሪ እሴት ማለት በፍጆታ እቃ ወይም በተጠቃሚ ወጪ ላይ የተመሰረተ ታክስ ሲሆን የሚሰበሰበውም ምርት ከውጭ ወደ አገር ውስጥ ሲገባ ወይም ማንኛውም ታክሱ የሚከፈልበት ዕቃና አገልግሎት ግብይት ሲካሄድበት፤በታክስ ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት ወይም በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሚሰበሰብ የታክስ አይነት ነው፡፡

ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚሰላው፤ ታክስ ከፋዩ ከደንበኞቹ የሚሰበሰበውን ተጨማሪ እሴት ታክስ /output tax/ በሚከፈልበት ጊዜ ምርቱን ለማምረት ወይም አገልግሎት ለመስጠት በግብዓትነት ለተጠቀመባቸው ጥሬ ዕቃዎች ግዢ ሲፈጽም የከፈለውን ተጨማሪ እሴት ታክስ በመቀነስ ይሆናል፡፡ ይህም ሂደት የመጨረሻው የምርቱ ወይም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ዘንድ እስኪደርስ ድረስ ይቀጥላል፡፡

ታክሱ፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበን ወይም መመዝገብ ያለበትን ሰው፣ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገባን ሰው እንዲሁም በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ሳይመዘገብ አገልግሎት የመሥጠት ሥራ ላይ የተሰማራን ማንኛውንም ሰው የሚመለከት አይነት ሲሆን፤ ይህ የሚመለከተው የሚከተሉትን መፈፀም ይኖርበታል፡-

ሀ. ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገብ

ለ. መዝገብ የመያዝ ግዴታ

ሐ. ግብይትን ለታክስ ሰብሳቢው መ/ቤት /ባለሥልጣን/ ማሳወቅ

መ. የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ /ካሽ ሬጅስተር/ መጠቀም

ተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የመኖሪያ ቤት(በዋናነት ለመኖሪያነት እንዲውል ታቅዶ የተሰራ ህንፃ)፣ ያገለገለ መኖሪያ ቤት ሽያጭ እና ኪራይ፣ የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚቀርብ ወርቅ ማስገባት እንዲሁም በሀይማኖት ድርጅቶች የሚሰጡ የአምልኮ ግልጋሎቶች (የኃይማኖት ተቋማት ለገቢ ማስገኛ የገነቧቸውን ህንጻዎችና የንግድ አገልግሎቶችን አይመለከትም)፣ የህክምና አገልግሎቶች፣ የትምህርት አገልግሎቶች፣ የኤሌክትሪክና የውሃ እና የመሳሰሉት ከታክሱ ነፃ የሆኑ ግብይቶች ሲሆኑ፤ ማንኛውም እቃ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገባበት ወቅት የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዳይጣልበት ካልተደነገገ በስተቀር የ15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚጣልበት ይሆናል፡፡

በዳንኤል ታደሰ

Add comment

We want to hear from you and strive to make our Website better and user friendly.

Please don't ask Questions here bcz there is a forum link for questions and answers since you may not get an answer from Feedback.


Security code
Refresh

Comments  

+1 #3 amanuel tewolde 2015-12-27 19:46
Hi Dani I wont motorcycle sport 400cc import from dubi how much tax
Quote
-1 #2 WebAdmins 2015-10-23 13:46
Quoting Girma Gebretsadik:
In the list of indirect taxes, you indicated that withholding is among the indirect taxes. Withholding is not a tax by itself. There is withholding for direct taxes such as business profit tax, employment income tax, dividend and interest. There is also withholding for VAT.

You are right Girma.
sorry for the mistake.
its been correct. Thank You!
Quote
#1 Girma Gebretsadik 2015-10-22 08:20
In the list of indirect taxes, you indicated that withholding is among the indirect taxes. Withholding is not a tax by itself. There is withholding for direct taxes such as business profit tax, employment income tax, dividend and interest. There is also withholding for VAT.
Quote
Visitors: Yesterday 8 | This week 119 | This month 625 | Total 430212

We have 623 guests and no members online