ኢ-ታክስ ምንድነው?

Posted in Know How

-ታክስማለት፡- ዘመናዊ ፈጣን እና ተደራሽነት ያለው ኢንተርኔት በመጠቀም ታክስን የማስታወቅ፣ ክፍያን የመፈፀም፣ የክሊራንስ አገልግሎት የማግኘት እና የታክስ ነክ ጥያቄዎችና ማብራሪያዎች ለማግኘት የሚረዳ አሰራር ከመሆኑም በላይ ግብር ከፋዬች የራሳቸውን ታክስ ነክ መረጃ በቀላሉ ማንበብ ወይም ማየት የሚችሉበት የኢነተርኔት አሰራር ነው፡፡

-ታክስ የሚያጠቃልላቸው አገልግሎት አይነቶች በሚከተሉት መልክ ቀርቧል፡፡

v  ኢ-ፋይሊንግ የግብር መረጃን ኤሌክትሮኒክስ በሆነ መልኩ የኢንተርኔት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመላክ አሰራር ስርዓት ነው፡፡  

v  ኢ-ፔይመንት ግብር ከፋይ ድርጅት ወደ ታክስ ባለሥልጣን መ/ቤት በአካል በመምጣት ሳያስፈልገው ከየትኛውም ቦታ ሆኖ የኢንተርኔት አገልግሎት በመጠቀም ወደ ተቋሙ ድህረገጽ በመግባት ቀደም ሲል በኢ-ፋይሊንግ በላከው መረጃ መሠረት ወደ ባንክ በመሄድ ክፍያውን በባንክ በኩል በተዘጋጀው የኢንተርኔት መስመር መሠረት ለታክስ ባለሥልጣኑ ክፍያ መፈፀም ሲሆን በዚህ መልክ ለከፈለው ክፍያም ደረሰኙ በኢንተርኔት አማካኝነት ወደ ድርጅቱ የሚላክለት የአሰራር ስርዓት ነው፡፡

v  ኢ-ክሊራንስ ግብር ከፋዩ ድርጅት የባለሥልጣኑ መ/ቤት ድረ-ገጽ በመጠቀም የታክስ ምላሽ ክሊራንስ ለመጠየቅ የሚያስችለው ከመሆኑም በላይ በወቅቱ ግብሩን የከፈለ እና ምንም አይነት የታክስ ክፍያ የሌለው ግብር ከፋይ በቀላል መንገድ የዓመታዊ ንግድ ፈቃድ ማደሻም ሆነ ሌሎች ክሊራንሶች በኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት የሚችልበት የአሰራር ስርዓት ነው፡፡

v  የታክስ ነክ መረጃ አገልግሎት ኢ-ታክስን ተጠቅሞ አንድ ግብር ከፋይ ድርጅት መጠየቅ የሚፈልጋቸውን ታክስ ነክ መረጃዎችና ማብራሪያዎች በቀላሉ ማግኘት የሚያስችለው ሲሆን ግብር ከፋዮች የስርዓቱ ተጠቃሚ እየሆኑ በሄዱ ቁጥር ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ጋር ያላቸው የስራ ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ እና የሚያቀራርብ በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታያለው የአሰራር ስርዓት ነው፡፡

 አንድ ግብር ከፋይ ለኢ-ታክስ ምዝገባ ምንምን ማሟላት ይጠበቅበታል፣

1.  Specification ያሟላ የኢ-ታክስ መጠቀሚያ ኮምፒውተር

2.  Processer Speed 3.2 GHZ ፍጥነቱ256 KBS እና ከዚያም በላይ የሆነ ብሮድባንድ ኢንተርኔት(EVDO)

3.  Adobe Reader 9 ወይም ከዚህ በላይ፣

4.  የኢንተርኔት መጠቀሚያ ኘሮግራም(Internet Browser) በቅርብ ጊዜ የመጣ መሆን ይኖርበታል፡፡

    ለምሣሌ፡- Internet Explorer 7ወይም የተሻለ

                   Mozilla:-Fire Fox ወይም በላይ

5.  በድርጅቱ የሚገኙ የሥራ ግብር የሚከፍሉ ሠራተኞች በሙሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6.  በመጨረሻ ድርጅቱ ከፊደል ተራ ቁጥር ሀ እስከ ሠ የተዘረዘሩት ካሟላ በኋላ ለመመዝገብ መስማማቱን የሚገልጽ የጽሁፍ ማረጋገጫ ለቅ/ጽ/ቤቱ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

-ታክስ መመዝገብ ያለበት ግብር ከፋይ ማን ነው?

ከዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ያለበት ማንኛውም ታክስ ነክ ክፍያዎች የሚከፍል እና የሚያስታውቅ ግብር ከፋይ ሲሆን በቅድሚያ ግን በቅደም ተከተላቸው እና በታክስ አከፋፈል ባህሪያቸው ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ እና ገቢ ያላቸው ቢሆኑ ለአሰራሩ ተመራጭ ይሆናል፤ በሂደት ግን ማንኛውም ግብር ከፋይ የዚህ ስርዓት ተጠቃሚ ቢሆን ትግበራውን ግቡ እንዲመታ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

አንድ ግብር ከፋይ የኢ-ታክስ ተመዝጋቢ በመሆኑ ቢያንስ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያገኛል፡-

v  ፈጣን የሆነ አገልግሎት ለመስጠት ያስችለዋል፣

v  አላስፈላጊ ጊዜ ገንዘብና የሰው ኃይል እንዳይባክን ያደርጋል፣

v  በተለይ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የደንበኞች እርካታ ከመፍጠሩም በላይ ለData Incoder  ይባክን የነበረውን ጊዜ እና የሰው ኃይል ለሌሎች ስራዎች እንዲውል ያደልጋል፡፡ በተጨማሪም የዕለት ገንዘብ ተቀባዬች እና የግብር ከፋይ መረጃ እና ክሊራንስ ክፍል ስራ በከፍተኛ ደረጃ ያቃልላል፡፡

 

Add comment

We want to hear from you and strive to make our Website better and user friendly.

Please don't ask Questions here bcz there is a forum link for questions and answers since you may not get an answer from Feedback.


Security code
Refresh

Comments  

-2 #10 Mihiret 2018-03-05 12:28
Keep it up, This service is one step forwarding for our country e-commerce and business transaction.
Quote
-2 #9 WebAdmin 2017-11-06 15:13
Quoting Muluget Nigussie:
very nice i am happy to be a part of it. is know available on the ground?

yes it is available.
Quote
+3 #8 Muluget Nigussie 2017-10-24 06:25
very nice i am happy to be a part of it. is know available on the ground?
Quote
+2 #7 getasew atinafu 2017-10-17 06:35
it is motivetor for ethiopian customers, keep it up;
Quote
#6 Gosayea 2015-12-25 06:56
it's one setep fowrward for modernaztion of taxation in ethiopia. but we star this proget in three branch of @revenue branch we need their progress to.
Quote
-3 #5 yibka 2015-11-03 13:29
it is very nice
Quote
-2 #4 kassaye 2015-10-12 11:36
that is good keep it up guys. i hope one day we will applay it in our branch.
Quote
-2 #3 belet 2015-10-08 08:11
:lol:
Quote
+3 #2 Mohammednur 2015-09-19 07:16
waw betam ds yilal bertulen!! ena lememzegeb bea internet bihon teru new
Quote
-1 #1 melaku bezie 2015-09-17 06:07
i am from mojo custom your information is very important.they are the motivetors to pay tax.
Quote
Visitors: Yesterday 8 | This week 119 | This month 625 | Total 430212

We have 222 guests and no members online